1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮፓው ኅብረትና ኤኮኖሚው

ቅዳሜ፣ ጥር 26 2004

የአውሮፓው ኅብረት የገንዘብ ሚንስትሮች፤ትናንት ብራሰልስ ውስጥ ባደረጉት ስብሰባ፤ የኅብረቱን የኤኮኖሚ ይዞታና የወደፊቱን ተስፋ በመገምገም በበርካታ አገሮች ላይ ያለውን የዕዳ ክምችት በመቀነስ፤

https://p.dw.com/p/13ppw
ምስል picture-alliance/dpa

ኤኮኖሚው እንዲሚያንሠራራ ለማድረግ የሚያስችሉ አሠራሮች ናቸው ያላቸውን በመቀየስ ተጠናቋል። በዚህ ዓመት የመጀመሪያ በሆነው ስብሰባ፤ ባለፈው የመሪዎች ጉባዔ ተነስተው ውሳኔ በተሰጠባቸውና ችግር ለሚያጋጥማቸው አገሮችየሚደርስ የአውሮፓ ኤኮኖሚ ማረጋጊያ፤ European Stability  Mechanism(ESM)የተሰኘውን የገንዘብ ተቋም ለመመሥረት በሚያስችለው ውል ላይ ከስምምነት ተደርሷል። የዚህ ተቋም ማቋቋሚያ ውል በሚቀጥለው ወር ከተፈረመ በኋላ በመጪው ሐምሌ ወር  ሥራውን ይጀምራል ተብሏል። በየሃገራቱ ያለውን የፋይናንስ አያያዝና የበጀት አመዳደብ ለመቆጣጠርና እርምጃ ለመውሰድ  በሚያስችል አሳሪ ህግ ላይ ሚንስትሮች  ተወያይተው የተስማሙ መሆናቸውም ተገልጿል።

ገበያው ንጉሤ

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሠ