1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮፓ ህብረትና የአፍሪካ ህብረት የጋራ ጉባዔ በብራስልስ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 23 2003

ዛሬ የአፍሪካና የአውሮፓ ህብረቶች በጋራ የሚያካሂዱት ጉባዔ በቤልጂየም ብራስልስ ተጀምሯል።

https://p.dw.com/p/RR3u
ምስል picture-alliance/ dpa

በኮሚሽነሮች ደረጃ እየተካሄደ ያለው ይህ ጉባዔ በዲሞክራሲ እና እድገት ላይ ሁለቱ አህጉራዊ ህብረቶች ሊኖራቸው ስለሚገባ ግንኙነት ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል። የአውሮፓ ህብረት ከአፍሪካ ሀገራት ጋር የንግድ ግንኙነት በመፍጠር ትልቁ አጋር እንደሆነ ይታወቃል። ይሁንና ሰሜን አፍሪካ ላይ የተቀጣጠለው የለውጥ አብዮት የአውሮፓ ህብረት ከአፍሪካ ጋር የሚኖረው ቀጣይ ግንኙነት ላይ ተጽእኖ ሳይፈጥር አይቀርም የሚሉ አስተያየቶችም ይሰማሉ። የብራስልሱን ወኪላችንን ገበያው ንጉሴን ጉባዔውን በተመለከተ በስልክ አነጋግሬው ነበር።

ገበያው ንጉሴ

መሳይ መኮንን

ሸዋዬ ለገሰ