1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮፓ ህብረትና ዩሮ የገጠመው ፈተና

ሐሙስ፣ የካቲት 11 2002

የ16 የአውሮፓ ሀገራት የጋራ መገበያያ ገንዘብ ዩሮ እንደ ግሪክ ባሉ ከፍተኛ የበጀት ቀውስ ውስጥ በወደቁ የዩሮ ቀጠና አባል ሀገራት ምክንያት የወደፊት ዕጣው ጥያቄ ምልክት ውስጥ ገብቷል ።

https://p.dw.com/p/M52z

ሲጀመር አንስቶ የጋራው ሸርፍ ዩሮ መንኮታኮቱ አይቀርም ሲሉ ያስጠነቅቁ የነበሩ የዩሮን የወደፊት ተስፋ ብሩህነት ተጠራጣሪ ወገኖች አሁንም አስቀድመን የተናገርነው ማስጠንቀቂያ ምልክት እየታየ ነው በማለት ላይ ናቸው ። ..................................... ዩናይትድ ስቴትስ የአውሮፓ ባንኮችን የገንዘብ ዝውውር ሰነዶች ማግኘት እንድትችልና በምትኩም በፀረ ሽብሩ ዘመቻ ለአውሮፓ ህብረት መንግስታት አጣራጣሪ ስለሆኑ ዕንቅስቃሴዎች የስለላ መረጃዎች እንድታቀብል ዩናይትድ ስቴትስ እና የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት መንግስታት በቅርቡ የተስማሙበትን አወዛጋቢ ውል የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ውድቅ አድርጓታል ። ተግባራዊ በሆነ በአስራ አንድ ቀናት ውስጥ በድምፅ ብልጫ የተጣለው ጊዜያዊ ስምምነት ሌላው የዝግጅታችን ትኩረት ነው ።

ሂሩት መለሰ ፣

አርያም ተክሌ