1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮፓ ባንኮች የገንዘብ ዝውውር መረጃ ያስነሳው ውዝግብ

ሐሙስ፣ ጥር 27 2002

የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሮች በዚህ ዓመት በህዳር ወር መጨረሻ ላይ ዩናይትድ ስቴትስ የአውሮፓን ባንኮች የገንዘብ ዝውውርን የሚመለከት መረጃ በይፋ እንድታገኝ የተስማሙበት ጊዜያዊ ፈቃድ ከዚህ ሳምንት ሰኞ አንስቶ ስራ ላይ ውሏል ።

https://p.dw.com/p/Lsxz
ምስል DW
ሚኒስትሮቹ ለአሜሪካን የሰጡት ይህ ፈቃድ ግን በአብዛኛዎቹ የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባላት ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም ። የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ ለዩናይትድ ስቴትስ መረጃ አሳልፎ ለመስጥት የተስማሙበት መንገድ ስምምነቱ የተደረገበት ወቅትና ሂደቱ እንዲሁም የግለሰቦችን ሚስጥር ተላልፎ እንዲሰጥ መፍቀዳቸውም በተለያየ አቅጣጫ ማወዛገቡን እንደቀጠለ ነው ። ከጎርጎሮሳውያኑ ታህሳስ 1 , 2009 ዓ.ም አንስቶ ከቀድሞው የላቀ የመወሰን ሥልጣን ያገኘው የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ስምምነቱን በመጪው ሳምንት በሚካሄድ ድምፅ አሰጣጥ ሳያፈርሰው እንደማይቀር እየተነገረ ነው ። ሂሩት መለሰ ፣ ነጋሽ መሀመድ