1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮፓ ኮሚሽን ሰብዓዊ ዕርዳታ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 9 2002

የአዉሮጻ ኮሚሽን በአፍሪቃ ቀንድ አገሮች በተለይም በኢትዮጽያ ሶማልያ ኬንያ እና ኡጋንዳ በድርቅ ምክንያት ለከፍተኛ ችግር ለተጋለጡ ሰዎች መርጃ የሚሆን 50 ሚሊዮን ይሮ የሚሰጥ መሆኑን ትናንት አስታዉቋል።

https://p.dw.com/p/L8CK
የአውሮፓ ኮሚሽን ቢሮምስል Barbara Cöllen/DW

የኮሚሽኑ የልማት እና የሰባዊ እርዳታ ኮሚሽን ትናንት በወጣዉ መግለጫ በዚህ አመት አብዛኛዉ የአፍሪቃ ቀንድ ክፍል ያገኘዉ የዝናብ መጠን ከዚህ ቀደም ያገኘዉ ከነበረዉ ከ 25 በመቶ የማይበልጥ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት 16ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የአካባቢዉ ነዋሪዎች አስቸኻይ እርዳታ እንደሚያገኙ እና ይህ የአሁኑ እርዳታ የአዉሮጻዉ ህብረት ለችግሩ የሚሰጠዉ ሰባዊ ምላሽ እንደሆነ መግለጹ ተጠቁሞአል። ዝርዝሩን ከብራስልስ ገበያዉ ንጉሴ

ገበያዉ ንጉሴ፣ አዜብ ታደሰ

ሂሩት መለሰ