1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮፓ የአቶም ኃይል ማመንጫዎች ደህንነት

ማክሰኞ፣ መጋቢት 13 2003

የጃፓን ፉኩሺማው የአቶም ኃይል ማመንጫ በኃይለኛው የመሬት መንቀጥቀጥ እና የውቅያኖስ ማዕበል ከባድ ጉዳት ከደረሰበት ወዲህ በተለያየ የዓለም ክፍል የሚገኙ የአቶም ኃይል አመንጪ ተቋማት ደህንነት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል ።

https://p.dw.com/p/RBVF
ምስል AP

በከባዱ አደጋ መንስኤ ኤሌክትሪክ ሲቋረጥ የፉኩሽማው የኃይል ማመንጫ ጋኖችን ግለት የሚያበርዱ ማቀዝቀዣዎች ስራቸውን ማቆማቸው የከፋ አደጋ ማስከተሉ ፣ እንዲሁም በአንዳንዶቹ ጋኖች ፍንዳታዎች ተከስተው ከተቋሙ መርዛማ ጨረር ማፈትለኩ ከአቶም ኃይል የሚያመነጩ አገራትን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ አንቅቷል ። በተለይ የአቶም ኃይልን በሰፊው ጥቅም ላይ ያዋሉት የአውሮፓ ሀገራት ከጃፓኑ አደጋ በኋላ ተቋሞቻቸው የሚገኙበት ሁኔታ እንዲፈተሽና እና የፉኩሽማው መሰል አደጋ እንዳይደርስ በጋራ ለመከላከል በሰፊው እየመከሩ ነው ።

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ