1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአየር ንብረት ጉባኤዉ ሂደት

ማክሰኞ፣ ኅዳር 28 2003

ከተጀመረ አንድ ሳምንት ያስቆጠረዉ በሜክሲኮ ካንኩን ከተማ የሚካሄደዉ የተመድ የአየር ንብረት ዓለም ዓቀፍ ጉባኤ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ይጠናቀቃል።

https://p.dw.com/p/QRpD
የጉባኤዉ ተሳታፊዎች በከፊልምስል picture alliance / dpa

ጉባኤዉን የምታስተናግደዉ አገር እንደአምናዉ ሁሉ የዘንድሮዉ ድርድር ሊቀመንበር ናት። አምና ዴንማርክ እንደነበረችዉ አሁን ደግሞ ሜክሲኮ። ያለፈዉ ዓመት ድርድር የተጠበቀዉን ያህል ዉጤት ባለማምጣቱ ከዘንድሮዉም ብዙ የሚጠበቅ ባይሆንም፤ በመጪዉ ዓመት ለሚካሄደዉ ጉባኤ ለስምምነት የሚያደርሱ ነጥቦች ይገኙበታል ተብሎ ይታሰባል። ከተለያዩ አገራትም በጉባኤ ለመሳተፍ ወደካንኩን የተጓዙ እንዳሉ ሁሉ ኢትዮጵያዉያን የአካባቢ ተፈጥሮ ተቆርቋሪዎችም ተገኝተዋል። አንድ ሳምንት ያሳለፈዉን የጉባኤዉን ሂደት ጠይቀናቸዋል። ዝርዝሩን ለመከታተል ከታች ማዳመጫዉን ይጫኑ!

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ