1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአየር ጠባይና የአየር ንብረት ለዉጥ

ማክሰኞ፣ የካቲት 8 2003

የአየር ንብረት ለዉጥ ከእለታዊ የአየር ሁኔታ መለዋወጥ ጋ የሚያገናኘዉ መሠረታዊ መገለጫ ቢኖርም አንድ ናቸዉ ማለት ግን አይደፈርም።

https://p.dw.com/p/R1Gf
ምስል Fotolia/Raldi Somers

ይህን ለማረጋገጥ ግን ተከታታይ ጥናቶች መካሄድ እንደሚኖርባቸዉ ነዉ ባለሙያዎች የሚናገሩት። የአካባቢ ተፈጥሮ ላይ የሚደርሱ የተለያዩ ሰዉሰራሽ ጉዳቶች በሂደት የሰዉ ልጅን ጤና እንደሚጎዱ ባለሙያዎች ያሳስባሉ። ለአየር ንብረት ለዉጥ ምክንያት የሚሆኑት የበካይ ጋዞች ከመጠን በላይ በከባቢ አየር ዉስጥ መበራከት፤ የሰዉ ሰራሽ ማዳበሪያና ጸረ ተባይ መድሃኒቶች በምግብ ዑደት ዞረዉ ወደሱ ልጆች መምጣታቸዉ ሲታሰብ፤ ጥንቃቄ ካልተደረገ ዉሎ አድሮ ጉዳቱ ሁሉንም ይነካል ሲሉም ያስጠነቅቃሉ።

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ