1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ«አይ ኤስ» ግድያ እና የኢትዮጵያ አስተያየት

ሰኞ፣ ሚያዝያ 12 2007

በሊቢያ እስላማዊ መንግሥት የተሰኘው አክራሪ ድርጅት 30 ኢትዮጵያውያንን በጥይትና በመቀላት የገደለበት የጭካኔ ተግባር ፣ እንዲሁም፣ በደቡብ አፍሪቃ በውጭ ዜጎች አንፃር በቀጠለው ሁከት በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለው የኃይል ተግባር በኢትዮጵያ ተወገዘ።

https://p.dw.com/p/1FBHq
Karte Äthiopien englisch

በደቡብ አፍሪቃው ሁከት አንድ ኢትዮጵያዊ ባለፈው ሳምንት በተጣለበት የቃጠሎ አደጋ ህይወቱ አልፋለች። የኢትዮጵያ መንግሥት: የኢትዮጵያ ተዋህዶ ኦርቶዶክስ የኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት እና የአፍሪቃ ሕብረት ኮሚሽን አረመኒያዊ እና ኢሰብዓዊ ሲሉ አውግዘውታል። የኢትዮጵያ መንግሥት ከነገ ጀምሮ የሶስት ቀናት ብሔራዊ ሀዘን አውጆዋል።

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ