1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዮዲን እጥረት፤ እንቅርት

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 8 2004

ሰዉነታችን ዉስጥ የሚገኙ ሴሎች የሚያመነጩዋቸዉ የተለያየ አገልግሎት የሚሰጡ ሆሮሞኖች ወይም ተፈጥሯዊ ንጥረ-ነገሮች አሉ። እነዚህ ተፈጥሯዊ ንጥረ-ነገሮች በየደረጃዉ በሚያደርጉት ዉህደትና መስተጋብር እንደየተግባራቸዉ የታሰበዉን እድገትና ለዉጥ በአካላችን ላይ ያስከትላሉ።

https://p.dw.com/p/15pav
ምስል DW-TV

በዚያዉ ልክ ከመጠን ሲያልፉ ወይም ሲያንሱ ደግሞ ችግር ይኖራል። ለምሳሌ በአዮዲን እጥረት ምክንያት ተግባሩ የሚስተጓጎለዉ የአንገት እጢ እንቅርት ሲያስከትል ይህም በመድሃኒት አለያም በቀዶ ጥገና ሊወገድ የሚችል የጤና ችግር ነዉ። አዮዲን የተሰኘዉን ንጥረነገር  ዉሃ ዉስጥም ሆነ ጨዉ ዉስጥ ተቀላቅሎ ሊወሰድ ይችላል። በቀን ሃያ ሚሊ ሊትር አዮዲን መዉሰድ ከተቻለ፤ የአንገት እጢ በአግባቡ እንዲሰራ በማድረግ የእንቅርትን ስጋትን ለማራቅ ይቻላል ተብሎ ይታመናል። ለመሆኑ እንቅርት ሴቶችን ብቻ ነዉ የሚያጠቃዉ ወይስ ወንዶችም ይታይባቸዋል? ሳምንታዊ መሰናዷችን ጤናና አካባቢ የባለሙያ ማብራሪያ ይዟል። ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ