የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ያማረረው የኤሌክትሪክ መቋረጥ
ረቡዕ፣ ግንቦት 5 2007ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በተደጋጋሚና ለረዥም ሰዓታት አንዳንዴም ለቀናት በሚደርሰው የኤሌክትሪክ መቋረጥ መማረራቸውን አስታወቁ ። ነዋሪዎቹ እንደሚሉት የኤሌክትሪክ መቋረጥ በዕለት ተዕለት ህይወታቸው፤ በንግድ እንዲሁም በምርት ሂደት ላይ አሉታዊ ጫና አሳድሮባቸዋል ። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበኩሉ ችግሩ በማሰራጫና በማከፋፈያ አቅም ውስንነት አንዲሁም በብልሽት ምክንያት መፈጠሩን ለዶቼቬለ አስታውቋል ። በበዙ ወጪም የማስፋፍትና የማሰራጫዎች የማሻሻል ሥራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውን ድርጅቱ ገልጿል ። የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረእግዚአብሄር እርእሩን ልኮልናል ።
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሄር
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ