1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መኢአድ እና ሰማያዊ በጋራ ሊወዳደሩ ነው

ማክሰኞ፣ መስከረም 23 2010

በዘንድሮው የአዲስ አበባ ምክር ቤት ምርጫ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ እና ሰማያዊ ፓርቲ በጋራ እንደሚወዳደሩ አስታውቀዋል።

https://p.dw.com/p/2l9qU
Äthiopien - Addis Abeba - City Churchill Road
ምስል DW/Y. Geberegziabehr

የምክር ቤት ምርጫ ዝግጅት በአዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዘንድሮ ለሚካሄደው የአዲስ አበባ አስተዳደር ምክር ቤት ምርጫ  ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆኑን አስታወቀ። ቦርዱ መረጃ የማሰባሰብ ሥራ ከሞላ ጎደል ማጠናቀቁን እና የምርጫ ቁሳቁሶችም እየተዘጋጁ መሆናቸውን ለዶቼቬለ ተናግሯል።

በዘንድሮው የአዲስ አበባ ምክር ቤት ምርጫ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ እና ሰማያዊ ፓርቲ በጋራ እንደሚወዳደሩ አስታውቀዋል። በ1997 የተደረገው ምርጫ ውጤት ባስከተለው ውዝግብ ምክንያት አዲስ አበባ በቦርድ ትመራ ስለነበረ ምርጫ የምታደርገው ከብሔራዊው ምርጫ በተለየ ዓመት ነው። የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝሩን ልኮልናል።


ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር 
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ