የአድዋ ድል መታሰቢያ
ዓርብ፣ የካቲት 23 2004ማስታወቂያ
116ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ዛሬ በመላው ኢትዮጵያ ተከብሯል። የዓድዋው ድል ለኢትዮጵያ ብቻ ሣይሆን ለመላው ጥቁር ሕዝብ መኩሪያና የነጻነት ትግል አርአያ ለመሆን መብቃቱ የሚታወቅ ነው። በዓሉ በአዲስ አበባው የአድዋ አደባባይ በይፋ ሲከበር በስፍራው የተገኘውወኪላችን ታድስ እንግዳው የሚከተለውን ዘገባ ልኮልናል።------ኢትዮጵያዉያን አርበኞች የኢጣሊያንን ቅኝ ገዢ ጦር አድዋ ላይ ድል ያደረጉበት በዓል ዛሬ በመላዉ ኢትዮጵያ ተከብሮ ዋላ።ንጉሰ ነገስት አፄ ሚኒልክ የመሯቸዉ ኢትዮጵያዉን ጀግኖች ኢትዮጵያን የወረረ ጠላታቸዉን አድዋ ላይ መትተዉ አሳፍረዉ የመለሱት በ1888።የዛሬዉ አንድ መቶ አስራ-ስድስተኛዉ የድል በዓል በተለይ አዲስ አበባ ዉስጥ በተለያዩ ሥነ-ሥነ ሥርዓቶች ነዉ የተከበረዉ።በበአሉ ላይ የተካፈሉ አባት አርበኞች እንዳሉት ግን የኑሮ ዉድነት የጡረታ ሕወታቸዉን መራር አድርጎባቸዋል።
ታደሰ እንግዳው
ነጋሽ መሐመድ
መሥፍን መኮንን
ሸዋዬ ለገሰ