1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአጎዋ ዓመታዊ ስብሰባ

ረቡዕ፣ ሐምሌ 29 2001

አፍሪቃውያን የየሀገሮቻቸውን ምጣኔ ሀብት ለማሳደግ ሙስናንና ወንጀልን በመዋጋት ረገድ ግንባር ቀደሙን ሚና እንዲጫወቱ ተጠየቁ ።

https://p.dw.com/p/J4Dv
ምስል picture alliance / dpa

የዩናይትድ ስቴትስዋ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን ዛሬ ናይሮቢ ውስጥ ለተከፈተው በእንግሊዘኛው ምህፃር AGOA በመባል ለሚጠራው ከሰሀራ በታች የሚገኙ የአፍሪቃ አገራት ምርቶቻቸውን ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ከቀረጥ ነፃ እንዲያስገቡ ለተመቻቸው የንግድ ዕድል መድረክ ስምንተኛ ስብሰባ ተካፋዮች እንዳሳሰቡት ብልሹ አስተዳደር ክፍለ ዓለሙን ወደኃላ እየጎተተ ነው ። በዚሁ ስብሰባ ላይ መንግስታቸው አፍሪቃን ለማገዝ ቆርጦ መነሳቱን ያሳወቁት ክሊንተን ሆኖም ዩናይትድ ስቴትስ አጋር እንጂ የበላይ ተቆጣጣሪ ልትሆን አትችልም ብለዋል ።

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ