1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአጼ ቴዎድሮስ መታስብያ

ሐሙስ፣ የካቲት 1 2004

«አልደፈር ብሎ ራሱን ገደለ፣ ጀግና ሰዉ ሰዉቶ ካሳ መች ከፈለ፣ ከመቅደላ በኩል ጩኸት በረከተ የሴቱን አናዉቅም ወንድ አንድ ሰዉ ሞተ፤ አባት እና እናቱ ካላንድ አልወለዱ አባ ታጠቅ ካሳ ያወንዱ ያዉ አንዱ፣ እጅ አልሰጥም ብሎ ለፈረንጅ ካቴና፣ ወድቆ ተሰበር ሽጉጠኡን ጠጣና»

https://p.dw.com/p/1407U
የአጼ ቴዎድሮስ መታስብያ በጎንደርምስል DW

«አልደፈርብሎ ራሱንገደለ፣ጀግና ሰዉ ሰዉቶካሳ መች ከፈለ፣ከመቅደላ በኩል ጩኸት በረከተ የሴቱን አናዉቅም ወንድ አንድ ሰዉ ሞተ፤አባት እና እናቱ ካላንድ አልወለዱ አባ ታጠቅ ካሳ ያወንዱ ያዉ አንዱ፣ እጅ አልሰጥም ብሎ ለፈረንጅ ካቴና፣ ወድቆ ተሰበር ሽጉጠኡን ጠጣና» ስለ ጀግናዉ አጼቴዎድሮስ እጅግ ብዙ ግጥም ተጽፎአል። ጫማ ሳይጫሙ አገር ለአገር ዞረዉ በመሳፍንት ተከፋፍላ የነበረች ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ እንደጣሩ እንደባከኑ መኖራቸዉ ታሪክ ያሳያል። አጼቴዎድሮስ እንድያ እንደባከኑ ለዉጭ ወራሪ እጄን አልሰጥም ብለዉ ራሳቸዉን በገዛ ሽጉጣቸዉ እረፍታቸዉን መርጠዋል።

አንዳንድ ጸሃፍቶች ቴዎድሮስ ለዝነኝነት ያበቃቸዉ ቁርጠኝነታቸዉ ሞትን መናቃቸዉ ድሎትን መራቃቸዉ ነ ዉ ሲሉ ይገልጻሉ። የቴዎድሮስን ታሪክ በርካታ ታላላቅ የአገራችን ደራሲዎች ጽፈዉ ለንባብ አብቅተዋል። ሎሪት ጸጋዪገብረ መድህን አቶ ብርሃኑ ዘሪሁን ለመድረክ ያበቁት የቴዎድሮስ ትያትር ተጥቃሽ ነዉ። «እጅህን ስጥ አለኝ ፈረንጅ፣ እጅ ተይዞ ሊወሰድ ምን እጅ አለዉ የሳት ሰደድ አያዉቅም ክንዴ እንደሚያነድ» በአዲስ አበባ መዘጋጃ ቤት እዉቁ ተዋናይ ፍቃዱ ተክለ ማርያም አጼ ቴዎድሮስን ተላብሶ የተጫወተዉ ገጸ- ባህሪ እንደኔ ሁሉ ሌሎችም በአይምሮአቸዉ ጠንካራ ማስታወሻን ተክሎ ያለፈ ይመስለኛል። የአጼ ቴዎድሮስ የትዉልድ ስፍራ የሆነችዉ ጎንደር በያዝነዉ አመት ጥር ወር መጀመርያ ለጥምቀት እና ከተማ ጎንደር በልዮ በምትዘጋጀዉ አመታዊ የካርኔቫል በአል ዋዜማ የአጼ ቴዎድሮስ መታሰብያ ሃዉልትን ሰርታለች። በኢትዮጵያዊ ባለሞያ የተቀረጸዉ የአጼ ቴዎድሮስ ሃዉልት ስራ የዛሪ አመት መጀመሩን እና በህዝብ እና በመንግስት ትብብር የሶስት መቶሃምሳ ሽ ብር ወጭ እንደጠየቀ የአራት ሜትር ቁመት እንደያዘ ተነግሮአል። ዛሪ ከደረስንበት በአጽናፋዊዉ ትስስር በኤሌክትሮኒክሱ ዘመን አለም በትስስሩ ኢምንት ሆና በቴክኖሎጂዉ መጥቃ በምትገኝበት ዘመን ላይ ሆነን የቀድሞ አባቶቻችን የስልጣኔ ፍቅር ምኞት ምን ያህል እንደነበር ስናጤነዉ ለህዝባቸዉ ለአገራቸዉ ብሎም ለአለም ሲሰሩት የነበረዉ ድካም መለካት ያዳግታል። እንደ አጼ ቴዎድሮስ የመሳሰሉቀ ደምት ወገኖች ያን ግዜ ሲመኙት የነበረዉ ህልማቸዉ እዉን ሆኖ ሳያዩት ቢያልፉም ህያዉ ስራቸዉ እዉን ሆኖ እኛም ታሪክን የምናጤንበት ሙዚየም ሃዉልትን ማቆማችን ይበል የሚያሰኝ ይመስለናል። የለቱን ሙሉዉን ክፍል መሰናዶ ያድምጡ!

አዜብታደሰ

ነጋሽ መሃመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ