1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፋር የፖለቲካ ፓርቲዎች ዉሕደት እና ዉዝግቡ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 17 2007

ሊቀመንበሩ እንደሚሉት የግንባሩ አባላት በቅርቡ ባደረጉት ጉባኤ የፓርቲያቸዉ ሕልዉና እንዲከስም ወስነዋል።የአፋር ነፃ አዉጪ ግንባር (ALF) አመራር አባላት ነን የሚሉ የአፋር ፖለቲከኞች ግን ዉሕደቱን እንደማይቀበሉት አስታዉቀዋል።

https://p.dw.com/p/1EANB
የአፋር የፖለቲካ ፓርቲዎች ዉሕደት እና ዉዝግቡ
ምስል picture-alliance/dpa

የአፋር ነፃ አዉጪ ግንባር ፓርቲ (ALFP) ከአፋር መስተዳድር ገዢ ፓርቲ ከአፋር ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ)ጋር መዋሐዱን አስታወቀ። የአፋር ነፃ አዉጪ ግንባር ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ከዳ አፎ አይዳ አይስ እንደገለፁት አንጋፋዉ ፓርቲቸዉ ከአብዴፓ ጋር የተዋሐደዉ አንድ ዓመት ከፈጀ ድርድር በሕዋላ ነዉ።ዉሕደቱ ሰመሮቢ ወረዳ በተደረገ ሥብሰባ መፅደቁን አቶ ከዳ አፎ አይዳ አይስ አስታዉቀዋል።ሊቀመንበሩ እንደሚሉት የግንባሩ አባላት በቅርቡ ባደረጉት ጉባኤ የፓርቲያቸዉ ሕልዉና እንዲከስም ወስነዋል።

የአፋር ነፃ አዉጪ ግንባር (ALF) አመራር አባላት ነን የሚሉ የአፋር ፖለቲከኞች ግን ዉሕደቱን እንደማይቀበሉት አስታዉቀዋል።ሥልክ የደወሉልን የግንባሩ ሥራ-አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ነን የሚሉ ፖለቲከኞች አንደገለፁልን፤ ሊቀመንበሩ ግንባሩ ከአብዴፓ ጋር ተዋሐደ የሚሉት የግንባሩን መሪዎችና አባላት ሳያማክሩ በራሳቸዉ ዉሳኔ ነዉ።የዉሕደቱን ስምምነት በመቃወም ለኢትዮጵያ ብሕራዊ ምርጫ ቦርድ አቤቱታ ማቅረባቸዉንም በሥልክ ያነጋገሩን የፓርቲዉ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የዞን አምስት የፅሕፈት ቤት ሐላፊ አቶ ያኩሙ በላዕቱ ሁሴይን ገልፀዉልናል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚ አብሔር

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ