1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃና የአውሮፓ የኤኮኖሚ ትስስር

ረቡዕ፣ ኅዳር 22 2003

አፍሪቃና የአውሮፓ ሕብረት ሕዝባዊት ቻይናን የመሳሰሉት በፍጥነት በመራመድ ላይ ያሉ ሃገራት የአፍሪቃን ክፍለ-ዓለም የተፈጥሮ ጸጋ መሻማት በያዙበት በአሁኑ ወቅት መሰናክል ገጥሞት የቆየ የኤኮኖሚ ትስስራቸውን ለማጠናከር ሰሞኑን ትሪፖሊ ላይ ባካሄዱት የመሪዎች ጉባዔ ተስማምተዋል።

https://p.dw.com/p/QMvX
ትሪፖሊምስል picture-alliance/dpa

ሆኖም የአውሮፓ ሕብረት ከአፍሪቃ አገሮች ጋር የኤኮኖሚ ሽርክና ውል ለማስፈን የሚያደርገው ግፊት እስካሁን የረባ ፍሬ አለመስጠቱ የሁለቱ ወገን የንግድ ግንኙነት ወደፊትም አስቸጋሪ ሆኖ እንደሚቀጥል የሚያመለክት ነው።
ለሁለት ቀናት የተካሄደው የትሪፖሊው የመሪዎች ጉባዔ ትናንት እንዳበቃ በወጣው የጋራ መግለጫ መሠረት የአፍሪቃን ዕድገት ለማፋጠን የአውሮፓውያኑን የመዋዕለ-ነዋይ አቅርቦት ከፍ ለማድረግና ንግዱንም ለማስፋፋት ነው የሚታሰበው። ጥያቄው ቃል ገቢር ይሆናል ላይ ነው። ሁለቱም ክፍለ-ዓለማት አፍሪቃና አውሮፓ ዓለምአቀፉ የፊናንስ ቀውስ ጥሎት ካለፈው ችግር ገና ሙሉ በሙሉ አልተላቀቁም።
በዚሁ ላይ የቻይናና መሰል በተፋጠነ ዕድገት ላይ የሚገኙ ሃገራት የመዋዕለ-ነዋይና የንግድ ተሳትፎ በአፍሪቃ መጠናከር በተለይም ለአውሮፓውያኑ ፈታኝ ነው የሆነው። ከዚህ አንጻር 60 ገጾችን ባቀፈ የጋራ የተግባር መርህ የተጠቃለለው ግብ ዕውን መሆን መቻሉን ማመኑ ቢቀር ካለፉት ልምዶች አንጻር የሚያድግት ነው። በአውሮፓ ሕብረትና በአፍሪቃ የንግድ ግንኙነት ሂደት፤ እንዲሁም በሕብረቱ የኤኮኖሚ ሽርክና ውል ግፊት ላይ ከዳንዲው ዩኒቨርሲቲ የዓለምአቀፍ ንግድ መምሕር ከዶር/መላኩ ደስታ ጋር ያደረግነውን ቃለ-ምልልስ ያድምጡ!
መሥፍን መኮንን

አርያም ተክሌ