1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃን ድህንት ለመቀነስ የተዘጋጀው የዓለም ባንክ የተግባር ዕቅድ

ዓርብ፣ መስከረም 13 1998

በአፍሪቃ የሚታየው ድህነትና ሥቃይ ከሌሎች የዓለም አካባቢዎች ሁሉ የከፋ መሆኑን የዓለም ባንክ ፕሬዚደንት ፖል ዎልፎቪትስ የባንኩን መሪነት ሥልጣን በተረከቡበት ጊዜ በማስታወቅ፡

https://p.dw.com/p/E0eK
ድህነትን የመታገሉ ተግባር ዋነኛው የድርጅታቸው ዓላማ እንደሚሆን መግለፃቸው የሚታወስ ነው። በዚህም የተነሣ አንድ የባንኩ ቡድን ይህንኑ ዓላማ ሀገድ ለማድረግ የሚያስችል አንድ የተግባር ዕቅድ አውጥቶዋል። ዕቅዱ የዓላም ባንክና ዓለም አቀፉ የገንዘብ መርህ ድርጅት፡ አይ ኤም ኤፍ አባል መንግሥታት ሚንስትሮች በሣምንቱ መጨረሻ በዋሽንግተን በሚሰበሰቡበት ጊዜ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
ለአፍሪቃ ትልቁ የልማት ርዳታ ሰጪ የሆነው የዓለም ባንክ በአህጉሩ ከሦስት መቶ የሚበልጥ ፕሮዤዎችን ያንቀሳቅሳል፤ 16,6 ሚልያርድ ዶላር ርኣታ ለመስጠትም ቃል ገብቶዋል። ፖል ዎልፎቪትስም በዕቅዱ ተግባር አማካይነትም የገንዘቡን ርዳታና ምክሩን ለማጠናከር ይፈልጋሉ። ምክንያቱም በአህጉሩ ሁነኛ የመሻሻል ሂደት ለማስገኘት እንደሚቻል ዎፎቪትስ ያምናሉና፤ ለዚሁ አባባላቸውም በርካታ የአፍሪቃ ሀገሮች ኤኮኖሚያቸውን ለማሳደግና ሕዝቦቻቸውን ተጠቃሚ ለማድረግ የቻሉበትን ርምጃ ዎልፎቪትስ እንደ ምሳሌ ጠቅሰዋል። ድህነትን ለመታገል ዘላቂ የኤኮኖሚ ሂደት ወሳኝ መሆኑን የሚያምኑት የዓለም ባንክ ፕሬዚደንት አፍሪቃውያቱ ሀገሮች ድህነትን ለመቀነስ በጀመሩት በዚሁ ጥረታቸው ላይ የዓለም አቀፉ ኅብረተ ሰብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው አስታውቀዋል።
የተግባሩ ዕቅድ የመንግሥታቱን አመራርና የኤኮኖሚ ዕድገት ጥያቄዎችን፡ በተለይም የግሉ ዘርፍ ሥራ በመፍጠሩና ድህነትን በመታገሉ፡ እንዲሁም፡ ለድሆቹ አዳዲስ ዕድል በፍጠሩ ረገድ ወሳኝ ሚና የሚጫወትበትን ሁኔታ ይመለከታል። ሕፃናት ነፃ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት የሚያገኙበትን ሁኔታ የመደገፍ፡ ለመሠረተ ልማቱ ተጨማሪ ወጪ የመመቡን፡ ኤድስና ወባን የመሳሰሉ በሽታዎችን የመታገሉን፡ እንዲሁም፡ እስከዛሬ በወጡ ዕቅዶች ሁሉ አዘውትረው የተረሱትና በልማቱ ሂደት ዘርፍ ላይ ወሳኝ ድርሻ የሚያበረክቱት ሴቶች ተጨማሪ ሚና የሚጫወቱበትን ድርጊት ያበረታታል።

ባለፈው ሰኔ ወር አራት የአፍሪቃ ሀገሮችን የጎበኙትና አህጉሩ በሀያ አንደኛው ምዕተ ዓመት የሚጠብቀውን ከባድ ሥራ የተመለከቱት ዎልፎቪትስ አህጉሩ የተስፋ አህጉር እንደሚሆን አስፋቸውን ገልፀዋል። ተፋጣኙን ዕድገት ልታስገኝ የምትችልበትን ፖለቲካ ተግባራዊ ታደርግ ዘንድ የዓለም ባንክ ለመርዳት አቅዶዋል። በተግባሩ ዕቅድ መሠረት፡ጋና ሴኔጋል ቡርኪና ፋሶና ሞዛምቢክ የመሳሰሉ ሀገሮች ደህና ብልፅግና የሚታይባቸው ሀገሮች ሆነው ይቆጠራሉ፡ ናይጀሪያ ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሬፑብሊክ ሱዳንና ኢትዮጵያ ደግሞ አዎንታዊውን የኤኮኖሚ የልማት ሂደት አሳይተዋል። ይወጣል በሚባለው የተግባር ዕቅድ አህጉሩ አጠቃላይ ኤኮኖሚያዊ ዕድገት ለማስገኘትና ድሆቹ የአህጉሩ ሀገሮችና ደህና የሚባሉትም ተጠቃሚ የሚሆኑበት ሁኔታን ለመፍጠር ታስቦዋል። በዕቅዱ መሠረት፡ የዓለም ባንክ ለመሠረተ ልማቱ - ብሎም - ለመንገድ ግንባታ፡ ለኃይሉ ምንጭ እና ለውኃ አቅርቦቱ ባንኩ አሁን የሚሰጠውን አንድ ነጥብ ስምንት ሚልያድርድ ዶላር በመጀመሪያ ወደ ሦስት ሚልያርድ ለማሳደግ አስቦዋል። በኤኮኖሚ ጠበብት ግምት መሠረትም፡ ባለፈው ዓመት አምስት ነጥብ እድ የነበረው የአህጉሩ ኤኮኖሚያ ዕድገት በሚቀጥለው ዓመት ወደ ሰባት ነጥብ ከመቶ ከፍ እንደሚል ተመልክቶዋል። የአፍሪቃ መንግሥታት ለመሠረተ ልማቱ በያመቱ አሥራ ሰባት ሚልያርድ ዶላር ወጪ መመደብ ይገባቸዋል፤ የትምህርቱ፡ የጤናውና የአመጋገቡ ዘርፋቸውን እንዲያሻሽሉ፡ እንዲሁም፡ ሥር የሰደደውን ሙስና ለማጥፋት ቆርጠው መታገል ይኖርባቸዋል።