1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ህብረት በICC ላይ ያሳለፈዉ ውሳኔ

ቅዳሜ፣ ጥቅምት 2 2006

የአፍሪቃ ሕብረት አባል ሀገራት መሪዎች ከዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት (ICC) ጋ ስለሚኖራቸው ግንኙነት የጋራ አቋም ለመያዝ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ሲወያዩ ውለዋል።

https://p.dw.com/p/19ybb
ADDIS ABABA, ETHIOPIA - MARCH 18: A plaque stands outside the headquarters complex of the African Union (AU), which was a gift by the government of China and completed in 2012, on March 18, 2013 in Addis Ababa, Ethiopia. Ethiopia, with an estimated 91 million inhabitants, is the second most populated country in Africa and the per capita income is $1,200. (Photo by Sean Gallup/Getty Images)
ምስል Getty Images

የኢትዮጵያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፤ የአፍሪቃ ሕብረት ትናንት በተደረገዉ ልዩ የሚኒስትሮች ሥብሰባ ፤ የዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት፤ በኬንያዉ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ላይ የተጀመረዉ ክስ፤ ፍጹም ተቀባይነት የለዉም ሲል መስማማቱን ገለጹ። አፍሪካ የዓለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት መሞከሪያ መሆን የለባትም ያሉት የአፍሪቃ ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች፤ በኬንያታ ላይ የተጀመረዉ የፍርድ ሂደት፤ ኬንያ አሸባሪዎችን ለመዋጋት የጀመረችዉን ስራዋን የሚያደናቅፍ ተግባር ነዉ ሲል፤ የአፍሪቃዉ ሕብረት፤ ማሰቡን፤ የኢትዮጵያዉ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲና ሙፍቲ ለፈረንሳዩ ዜና ወኪል በስልክ ገልፀዋአል። በዘር ጭፍጨፋ ወንጀል ጉዳይ አፍሪቃዉያን ፤ በአፍሪቃ ሕብረት የተደገፈ ፍርድ ቤት እንዲዳኙ እንጂ በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት ዴንሃግ ድረስ እንዲቀርቡ መገደድ የለባቸዉም ሲል ምክር ቤቱ፤ ሃሳብ ማቅረቡም ተያይዞ ተዘግቧል። የአፍሪቃ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በደረሱበት በዚህ አቋም ላይ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ጉባኤ የተቀመጡት የአፍሪካ መሪዎችም ይደግፉታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በስፍራው ጉባኤውን ከተከታተለው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ጋ የተደረገውን አጭር ቃለ መጠይቅ ከዚህ በታች ያገኙታል

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ልደት አበበ