1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ህብረት የዳርፉር ሰላም አስከባሪ ጓድ አዳጋች ተልዕኮ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 22 2002

በዳርፉር ከተመድ ሰላም አስከባሪ ጓድ ጎን የተሰማራው የአፍሪቃ ህብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል ከሽምቅ ተዋጊዎች በሚሰነዘርበት ጥቃት የተነሳ ተልዕኮውን በማከናወኑ ተግባሩ ላይ እክል እክል እየገጠመው መሆኑን ህብረቱ አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/O5jL
ምስል AP

እንደሚታወሰው የሽምቅ ተዋጊዎች ከጥቂት ጊዜ በፊት በምዕራብ ዳርፉር ነርቲቲ ጦር ሰፈር ዘልቀው በመግባት በከፈቱት ተኩስ ሶስት የርዋንዳ ወታደሮች ሲገደሉ፡ አንዱ በካባድ አቁስለዋል። ህብረቱ የሚሰነዘርበትን ጥቃት ተቋቁሞ ግዳጁን ለመወጣት ሲል አዲስ ስልት እየነደፈ መሆኑን ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ያነጋገራቸው የአፍሪቃ ህብረት የጸጥታ እና የሰላም ኮሚሽነር አምባሳደር ራምታን ላማምራን ገልጸዋል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሀመድ