1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ሕብረትና የሶማሊያ ሠላም

ዓርብ፣ ኅዳር 8 2004

ኬንያ ደቡቡ ሶማሊያ ከሚዋጋ ጦሯ ሌላ የሠላም አስከባሪ መለዮ ያጠለቀ ጦር ለማዝመት እንደምትፈልግ አስታዉቃለች።የኢትዮጵያ አቋም አለየም።

https://p.dw.com/p/RxCQ
የአፍሪቃ ሕብረት ጦር-ሞቃዲሾምስል AP

የአፍሪቃ ሕብረት ወደ ሶማሊያ ለማዝመት ላቀደዉ ሰወስት ሺሕ ተጨማሪ ሠላም አስከባሪ ሠራዊት አባል ሐገራት ወታደሮች እንዲያዋጡ ለማግባባት የሚያደርገዉን ጥረት እንደቀጠለ ነዉ።የሕብረቱ የሠላምና የፀጥታ ኮሚሽን ትናንት አዲስ አበባ ዉስጥ ባደረገዉ ሥብሰባዉ እስካሁን ሞቃዲሾ ጦር ያሰፈሩት ዩጋንዳና ቡሩንዲ ተጨማሪ ወታደሮች ለማዋጣት መፍቀዳቸዉን ሲያስታዉቅ፥ ጂቡቲ አንድ ሻለቃ ጦር ለማዝመት ቃል መግባቷን ገልጧል።ኬንያ ደቡቡ ሶማሊያ ከሚዋጋ ጦሯ ሌላ የሠላም አስከባሪ መለዮ ያጠለቀ ጦር ለማዝመት እንደምትፈልግ አስታዉቃለች።የኢትዮጵያ አቋም አለየም።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ ዝር ዝር ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ