1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ሕብረት ዕቅድና ትችቱ

ማክሰኞ፣ ጥር 26 2007

ተንታኞቹ እንደሚሉት ለሶማሊያ ከሃያ-ሁለት ሺሕ በላይ ጦር ያዘመተዉ የአፍሪቃ ሕብረት የናጄሪያንና የአካባቢዋ ሠላም በ7500 ወታደሮች ይከበራል ብሎ ማሰቡ እንቆቅልሽ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1EUyG
ምስል Reuters/Afolabi Sotunde

የአፍሪቃ ሕብረት የናጀሪያዉን እስላማዊ አክራሪ አማፂ ቡድን ቦኮ ሐራምን የሚወጋ 7500 ጦር ለማዝመት ማቀዱ ትችት ገጥሞታል። የፖለቲካ እና የወታደራዊ ጉዳይ ተንታኞች እንደሚሉት የአፍሪቃ ሕብረት ሊያዘምት ያቀደዉ ሠራዊት ከናጀሪያ አልፎ የአካባቢዉን ሐገራት የሚያሰጋዉን ቦኮ ሐራምን ለመዉጋት በቂ አይደለም። ተንታኞቹ እንደሚሉት ለሶማሊያ ከሃያ-ሁለት ሺሕ በላይ ጦር ያዘመተዉ የአፍሪቃ ሕብረት የናጄሪያንና የአካባቢዋ ሠላም በ7500 ወታደሮች ይከበራል ብሎ ማሰቡ እንቆቅልሽ ነዉ። የናጄሪያ መንግሥትም ዘማቹን ጦር ለመቀበል መፍቀዱ ገና በዉል አልታወቀም።የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለ ሚካኤል የሚከተለዉን ዘገባ ልኮልናል።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ