1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ሳምንት በፓሪስ

ሐሙስ፣ ግንቦት 18 2008

በአየር ለዉጥ ሳብያ ዘንድሮ ወደ 36 ሚሊዮን የሚሆኑ ሕዝቦችዋ ለረኃብ የተጋለጡባት አፍሪቃ በአጠቃላይ 1.2 ቢሊየን የሚሆነዉ ህዝብዋ ከግማሽ በላይ የሚሆነዉን ቁጥር የሚሸፍኑት ሴቶች ሲሆኑ ፤ ሴቶች በአየር ንብረት ለዉጥ ችግር ከፍተኛ ተጋላጭ መሆናቸዉን መረጃዎች ያመለክታሉ።

https://p.dw.com/p/1Iuvv
Frankreich Paris Africa Week - UNESCO
ምስል DW/H. Turuneh

[No title]

ይህን አስመልክቶ በያዝነዉ ሳምንት ፓሪስ ፈረንሳይ ላይ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት «UNECO» ጽ/ቤት እየተከበረ በሚገኘዉ የአፍሪቃ ሳምንት የአፍሪቃ ሴቶች በአየር ንብረት ለዉጥ የተጋረጠባቸዉ ፈተናዎች በሚል መሪ ቃል የተለያዩ የአፍሪቃ ሃገራት የተሳተፉበት አዉደ ርዕይ እና ባዛርን ጨምሮ የተለያዩ ዝግጅቶች እየተካሄዱ ሲሆን በዚሁ ርዕስ ዙርያም በተካሄደዉ ጉባኤ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎችም ቀርበዋል። በአየር ንብረት ሳብያ ሴቶችና ልጃገረዶች የችግሩ ዋና ተጋላጮች የመሆናቸዉም ያህል ለአካባቢ ጥበቃም ሴቶች የጎላ ሚናም እንዳላቸዉ በዚሁ ጉባኤላይም ተወስቶአል።

ኃይማኖት ጥሩነህ

አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ