1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ቀንድ ሐገራት ዜጎች ስደት

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 9 2005

በተገባደደው የጎርጎሮሳዉያኑ 2012 ዓመት ብቻ 100000 ኢትዮጵያውያን ወደ የመን ተሰደዋል። ወደ ፊትም ኢትዮጵያ ዜጎቿን በስደት ምክንያት ማጣቷ እንደሚቀጥል ተነግሯል። የዚህ ስደት ምክንያት ግን በሶማሊያ እንደታየው ያለመረጋጋት እጦት ሳይሆን በሀገሪቷ በታየው የገቢ መጨመር ምክንያት ነው ይላሉ ሚስተር ፒተር ኪላንሶ፥

https://p.dw.com/p/174zy
Displaced Eritreans receive blankets at the Dibarwa secondary school, 35 kilometers (22 miles) south of Asmara, Thursday, June 8, 2000. The school shelters some 54,000 people displaced by fighting between Eritrea and Ethiopia. Eritrea acknowledged for the first time that it was asking resident Ethiopians to move into camps for their own protection. (AP Photo/Jean-Marc Bouju)
ስደት-ኤርትራምስል AP

የአፍሪቃ ቀንድ ከፍተኛ የዜጎች ስደት ከሚታይባቸው የዓለማችን ሥፍራዎች ውስጥ ግንባር ቀደሙ ነው። በአፍሪቃ ቀንድ ሀገራት መካከልና ከሀገራቱ ውጭ ስለሚታየው ስደት የወደፊት ሁኔታ ላይ አንድ  የዴንማርክ የስደተኞች ድርጅት በቅርቡ ጥናት አድርጓል። በዚህም ጥናት መሠረት በሶማሊያ መረጋጋት ዳግም ከሰፈነ   በሌሎች ሀገራት የሚገኙ የሶማሊያ ዜጎች ሊመለሱ እንደምችሉ ተገልጿል። በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ምክንያት  የኢትዮጵያና ኤርትራ ዜጎች ስደት እንደሚቀጥል ጥናቱ ተጠቁሟል።  ገመቹ በቀለ በዴንማርክ የስደተኞች ድርጅት የአፍሪቃ ቀንድና የየመን ስደተኞች ተጠሪ ጋር  ያደረገውን ቃለምልልስ አቀናብሮ ያዘጋጀውን ያቀርባል።

ሶማሊያ፣ ኤርትራና ኢትዮጵያ ሶስቱም በስደት በየዓመቱ ብዙ ዜጎቻቸውን የሚያጡ  ሀገራት ናቸው። የነኚህ ሀገራት የስደተኞች ሁኔታ ወደ ፊት፣  ማለትም በ17 ዓመታት ውስጥ፣ ወዴት ያመራ እንደሆነ ለማየት በኢንግሊዘኛ ምህጻር DRC  የተሰኘው የዴንማርክ የስደተኞች ድርጅት ጥናት አድርጓል። በጥናቱም መሠረት ከሶማሊያ ውጭ በተለይም በኬኒያ፣ በኢትዮጵያና በየመን የሚገኙ ስደተኞች፣ የሶማሊያ የጸጥታ  ሁኔታ ከተለወጠ ሀገራቸው መመለስ ይፈልጋሉ። በነኚህ ሶስት ሀገራት ብቻ አንድ ሚሊዮን የሚሆኑ ወደ ሶማሊያ መመለስ የሚፈልጉ ስደተኞች እንዳሉ ተገልጿል።  ሆኖም እነኚህ ስደተኞች ወደ ሶማሊያ ለመመለስ የሚያስችላቸው ምቹ ሁኔታ የለም ይላሉ በዴንማርክ የስደተኞች ድርጅት የአፍሪቃ ቀንድና የየመን ስደተኞች ጉዳይ ተጠሪ ፒተር ክላንሶ፣

«ዜጎችን ከመከላከልና ህግን ከማስከበር  አንጻር አሁንም ብዙ የማያስተማምኑ ጉዳዮች በሶማሊያ ይገኛሉ። ልጆችን ወደ ትምህርት ከመላክና የእለት ጉርስን ከማግኘት አንጻር ያሉ ችግሮችም ስደተኞች ወደ ሶማሊያ ለመመለስ እንዲነሳሱ አያበረቱዋቸውም።»

ሶማሊያውያን ስደተኞች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የሚደረግ ጥረት ብዙ ዓመታትን ሊወስድ ይችላል። እንደ ሚስተር ክላንሶ፤ ለኑሮ የተመቻቹ ሁኔታዎች እስኪፈጠሩ ድረስ ወደ ሀገራቸው የሚመለሱ ሶማሊያውያን ብዙ ይሆናሉ ብሎ መገመት አዳጋች ነው።

በኤርትራ፣ በፖሊቲካዊና ኢኮኒሚያዊ  ችግሮች  ምክንያት በተለይም ወጣቶች ወደ ኢትዮጵያ፣ ወደ መካከለኛው ምስራቅ እንዲሁም  ወደ ምዕራብ ሀገራት የተሻለ ኑሮ ፍለጋ እንደሚሰደዱ ተገልጿል።

እየተገባደደ ባለው የፈንጆች ዓመት ብቻ 100,000 ኢትዮጵያውያን ወደ የመን ተሰደዋል። ወደ ፊትም ኢትዮጵያ ዜጎቿን በስደት ምክንያት ማጣቷ እንደሚቀጥል ተነግሯል። የዚህ ስደት ምክንያት ግን በሶማሊያ እንደታየው ያለመረጋጋት እጦት ሳይሆን በሀገሪቷ በታየው የገቢ መጨመር ምክንያት ነው ይላሉ ሚስተር ፒተር ኪላንሶ፥

«እጅግ በጣም ድሃ ከሆንክ መሰደድ አትችልም። ምክንያቱም ለመሰደድ የሚያስችልህ አቅም የለህምና። ግን ትንሽ ገንዘብ ካለህ መሰደድ ትችላለህ። ኢትዮጵያ ውስጥ የምናየው ይህንን ነው። ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ የታዩ የኢኮኖሚ እድገቶች አበረታች ነበሩ። ሰዎችም መጠኑ ከበፊቱ በትንሹ ከፍ ያለ ገንዘብ እያገኙ ነው። ያ ደግሞ ስደትን እንደ አንድ አማራጭ እንዲወስዱ ያደርጋቸዋል።»

ይህ ስደት ለብዙ ኢትዮጵያውያን ከድህነት ለመውጣት ፈጣኙ መንገድ ነው። በሚሰደዱበት ሀገራት ውስጥ የሚደርስባቸው የመብት ጥሰትና እንግልትም ከዚህ ጋር ተያይዞ በብዛት የሚሰማ ዜና ሆኗል። በቅርቡ በየመን የታየውን የፖሊቲካ አለመረጋጋት ተከትሎ ብዙ ኢትዮጵያውያን ለስቃይ መጋለጣቸው ተነግሯል። በሌሎችም የአረብ ሀገራት ቢሆን በተለይም በኢትዮጵያውያን ሴቶች ላይ የሚደርሰው ጥቃትና የመብት ጥሰት ተበራክቷል። ይህን የመብት ጥሰት ለመከላከል የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ  ሚና ትልቅ ነው ይላሉ ፒተር ክላንሶ፣

« በነኚህ ሀገራት በስደተኞች ላይ የሚደርስ ብዙ የህግ ጥሰትና ብዝበዛ ይታያል። እንደሚመስለኝ፤ መልካሙ መንገድ በግንባታ ኢንዱስትሪና በቤት ውስጥ ሥራ የሚታየውን ብዝባዥ አሰራር እንዲቀንሱ  ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በነኚህ ሀገራት ላይ ጫና ቢያደርግ ነው።»

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጫና ምናልባት ለውጥ ሊያመጣ ይችላል። ከዛ በተጓዳኝ ግን የአፍሪቃ ቀንድ መንግስታትም በሀገራቱ መካከል የሚካሄደውን የስደተኞች ሁኔታ ወደ አዎንታዊ ለውጥ ለመቀየር እርምጃ መውሰድ  እንዳለባቸው ሚስተር ፒተር ይናገራሉ፤

«ሥራ ከመፍጠር አንጻር ስደተኞች ለሀገራቱ ኢኮኖሚ ያላቸው ተፈላጊነት ላይ መንግስታቱ  የጋራ መረዳዳት ላይ መድረስ አለባቸው።  መንግስታቱ የጋራ ድንበሮቻቸው ላይ በሚታዩ የስደተኞች እንስቅቃሴ ላይ መሠረታዊ የጋራ መመሪያ ሊያወጡ ይገባል።

በስደት ምክንያት በበአውሮፓና በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙ የሀገራቱ ዜጎች፣ የገንዘብ ፍሰትን ከማበረታታት አንጻር ለሀገራቱ የሚያስገኙት ኢኮኖሚያዊ ጥቅም በቀላሉ እንደማይታይ ይነገራል።   በቅርቡ በሶማሊያ እንደታየው በአውሮፓና አሜሪካ የሚገኙ የአፍሪቃ ቀንድ ተወላጆች ሀገሮቻቸው በሚያደርጉት እንቅስቃሴ እንዲሳተፉ ምቹ መንገድ ቢመቻችላቸው የተሻለ ለውጥ እንደሚመጣ ይታመናል።

Refugees walk around the Dollo Ado refugee camp, Ethiopia, Thursday, July 7, 2011. The worst drought in the Horn of Africa has sparked a severe food crisis and high malnutrition rates, with parts of Kenya and Somalia experiencing pre-famine conditions, the United Nations has said. More than 10 million people are now affected in drought-stricken areas of Djibouti, Ethiopia, Kenya, Somalia and Uganda and the situation is deteriorating, (AP Photo/ Luc van Kemenade)
ስደት-ሶማሊያምስል AP
Refugees sit outside in an open area as there is lack of tents at the Dollo Ado refugee camp, Ethiopia, Thursday, July 7, 2011. The worst drought in the Horn of Africa has sparked a severe food crisis and high malnutrition rates, with parts of Kenya and Somalia experiencing pre-famine conditions, the United Nations has said. More than 10 million people are now affected in drought-stricken areas of Djibouti, Ethiopia, Kenya, Somalia and Uganda and the situation is deteriorating, (AP Photo/ Luc van Kemenade)
ስደት-ኢትዮጵያምስል AP

ገመቹ በቀለ

ተክሌ የኋላ