1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ቀንድ ረሐብና ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ

ረቡዕ፣ መስከረም 10 2004

ሐላፊዉ እንደሚሉት ኢትዮጵያንና ኬንያ ለደረሰዉ አደጋ የተሰጠዉ ምላሽ ወቅቱን የጠበቀ ነዉ።የሶማሊያዉ ግን የችግሩ ክፋትና ጥልቀት ለጋሾች ርዳታ ለማቅረብ የሚያደርጉትን ጥረት አክብዶባቸዋል

https://p.dw.com/p/Rn2R
ረሐብ በሶማሊያምስል dapd

የአፍሪቃ ቀንድ ሕዝብን ለረሐብ ያጋለጠዉ ችግር ሊከሰት እንደሚችል አስቀድሞ ጠቁሞ እንደነበር የዩናይትድ ስቴትሱ የረሐብ አደጋ ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ማዕከል አስታወቀ።የተቋሙ የመርሐ-ግብር ተጠሪ ጆን ሺቺታኖ እንደሚሉት አደጋዉ ሊከሰት እንደሚችል መስሪያ ቤታቸዉ የሚመለከታቸዉን ወገኖች ከስድስት ወር በፊት አስጠንቅቆ ነበር።ሐላፊዉ እንደሚሉት ኢትዮጵያንና ኬንያ ለደረሰዉ አደጋ የተሰጠዉ ምላሽ ወቅቱን የጠበቀ ነዉ።የሶማሊያዉ ግን የችግሩ ክፋትና ጥልቀት ለጋሾች ርዳታ ለማቅረብ የሚያደርጉትን ጥረት አክብዶባቸዋል።የዋሽንግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ሺቺታኖን አነጋግሮ የላከልን ዘገባ አለ።

አበበ ፈለቀ

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ