1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ኅብረት እና ጀርመን በዓመታዊ የሁለትዮሽ የምክክር መድረክ

ዓርብ፣ መስከረም 26 2010

ለአፍሪካ ልማት አዲስ አጋርነት (NEPAD) በኩል ገቢራዊ የሚሆነውን ክኅሎት ለአፍሪቃ የተባለ መርኃ-ግብር (Skills Initiative for Africa) በገንዘብ እንደምትደግፍም ጀርመን አረጋግጣለች።

https://p.dw.com/p/2lOnj
African Union Hauptquartier in Addis Abeba
ምስል AFP/Getty Images/J. Vaughan

የአፍሪቃ ኅብረት እና የጀርመን ትብብር


አፍሪቃ በፍጥነት እያደገ ለመጣው ወጣት የሕዝብ ቁጥሯ በቂ የሥራ እድል መፍጠር እንድትችል ጀርመን እገዛ እንደምታደርግ አስታወቀች። ለአፍሪካ ልማት አዲስ አጋርነት በእንግሊዘኛ ምኅጻሩ (NEPAD) በኩል ገቢራዊ የሚሆነውን ክኅሎት ለአፍሪቃ የተባለ መርኃ-ግብር (Skills Initiative for Africa) በገንዘብ እንደምትደግፍም ጀርመን አረጋግጣለች። ክኅሎት ለአፍሪቃ የተባለው መርኃ-ግብር በቴክኒክ ሥልጠናና ትምህርት ላይ ያተኩራል። በዚህ መርኃ ግብር መሰረት የገንዘብ ድጎማ የሚያገኙት የግል ኩባንያዎች፤ የቴክኒክ፤ የሙያ፤ የትምህርት እና የሥልጠና ማዕከላት ናቸው። የአፍሪቃ ኅብረት ድረ-ገፅ ላይ የወጣ መግለጫ እንደሚጠቁመው ከተመረጡ አገራት የመንግሥት ተቋማትም በመርኃ-ግብሩ መሰረት የገንዘብ ድጋፍ ያገኛሉ። የተመረጡት አገራት ደቡብ አፍሪቃ፤ ኬንያ፤ቱኒዝያ፤ካሜሩን እና ናይጄሪያ ናቸው። የኤኮኖሚ ሽግግር፤ የወጣቶችን ክኅሎትን ማሳደግ፤ የተሻለ መሰረተ-ልማት እና ለአፍሪቃ የንግድ ትሥሥር የሚያገለግል ግዙፍ ገበያ ለወጣቶች ተስፋን ለመፍጠር እና ፍልሰትን ለመግታት ሁነኛ መንገዶች ናቸው ተብሏል። 
ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሐመድ