1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ እና የአዉሮጳ ኅብረት ጉባኤ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 19 2010

የአፍሪቃ እና የአዉሮጳ ኅብረት የጋራ ጉባኤ ከነገ ጀምሮ ለሁለት ቀናት አቢዣ ኮት ዴቩዋር ላይ ይካሄዳል። በጉባኤዉ ላይ የአፍሪቃ ሃገራት መሪዎች በሙሉ እንደሚገኙ ይጠበቃል። ከብራስልስም የአዉሮጳ ኅብረት ባለስልጣናት እና የአባል ሃገራት መሪዎችም ለአምስተኛ ጊዜ በሚካሄደዉ የኅብረቱ እና የአፍሪቃ ሃገራት ጉባኤ ላይ ይገኛሉ።

https://p.dw.com/p/2oPKy
Elfenbeinküste Abidjan Goethe Institut
ምስል DW/S. Blanchard

ከከዚህ በፊቶቹ ስብሰባዎች የተለየ እንደሚሆን ኅብረቱ እየገለፀ ነዉ፤

 

የአፍሪቃ ሃገራት መሪዎች እና የኅብረቱ ባለስልጣናት በተለይ ስደተን በመግታቱ ሃሳብ ላይ ተደጋጋሚ ዉይይቶች እና ስብሰባዎች አካሂደዋል። የአዉሮጳ ኅብረት መሪዎች ጉባኤዉ ከዚህ በፊት ከተካሄዱት ስብሰባዎች የተለየ እንደሚሆን ሲናገሩ ተደምጧል። ልዩነቱ በምን ይሆን? ከስብሰባዉስ ምን ዉጤት ይጠበቃል? የዕለቱ የአዉሮጳ እና ጀርመን መሰናዶ በዚህ ላይ ያተኩራል። ከብራስልስ ዘጋቢያችን ገበያዉ ንጉሤ አዘጋጅቶታል።

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ