1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ኮሚሽን ፕሬዝዳት ምርጫ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 11 2004

በሥልጣን ላይ ያሉት የአፍሪቃ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳት ዤን ፒንግ የያዙትን ሥልጣን ለተጨማሪ ዘመነ-ሥልጣን ይቀጥሉ ወይም በሌላ ይተኩ የሚለዉ ሐሳብ የአፍሪቃ መሪዎችን አላግባባም።

https://p.dw.com/p/14ODt
Symbolbild Finanzkrise in Afrika Copyright: AP/DW Fotomontage
ምስል AP/DW Fotomontage


የአፍሪቃ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳት ለመምረጥ ኮተኑ-ቤኒን ዉስጥ ባለፈዉ ቅዳሜ ተሰይሞ የነበረዉ የአሐጉሪቱ አምስት ቀጣና ተወካዮች ስብሰባ በቀጠሮ አበቃ።የሰሜን፥ የምሥራቅ፥ የምዕራብ፥ የደቡባዊና የማዕከላዊ አፍሪቃን የወከሉት መሪዎችና ባለሥልጣናት ዉይይት ባለፈዉ ጥር አላግባባ ያለዉን የአዲስ ኮሚሽን ፕሬዝዳት ምርጫ እልባት ለማግኘት ያለመ ነበር።አሁን በሥልጣን ላይ ያሉት የአፍሪቃ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳት ዤን ፒንግ የያዙትን ሥልጣን ለተጨማሪ ዘመነ-ሥልጣን ይቀጥሉ ወይም በሌላ ይተኩ የሚለዉ ሐሳብ የአፍሪቃ መሪዎችን አላግባባም።የኮቶኑ ተሰብሳቢዎች ጉዳዩን አጥንተዉ ከሰወስት ወር በሕዋላ ማሊ ለሚደረገዉ ጉባኤ የሚያቀርቡ ሐገራትን ወክለዉ ተለያይተዋል።ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ ዝር ዝሩን አጠናቅሮታል።

ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ

ነጋሽ መሀመድ

ሒሩት መለሰ