የአፍሪቃ ወጣት መሪዎች በዋይት ሃዉስ
ሐሙስ፣ ሐምሌ 30 2007ማስታወቂያ
ከ 30 ሺህ ተወዳዳሪዎች መካከል ተመርጠዉ የመጡት እነዙህ ወጣቶች 500 መሆናቸዉ ነዉ የተነገረዉ። የአፍሪቃዉያን ወጣት መሪዎች ዉጥን ማጎልበቻ መረብ በመባል የሚታወቀዉ ዓመታዊ መረሃ -ግብር በፕሬዚዳንት ኦባማ አማካኝነት ከተጀመረ ሁለት ዓመታትን አስቆጥሮአል። መሰል ማዕከል በአፍሪቃ ጋና ከተማ የተከፈተ ሲሆን ሌሎች ተጨማሪ ማዕከሎች በዓመቱ መጨረሻ እንደሚከፈቱ ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል። በቀድሞዉ የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚዳንት በኔልሰን ማንዴላ ስም የተሰየመዉና የማንዴላ አርዓያነት የተባለዉ ይህ ተቋም ሶስት ስልጠናዎችን በማኅበራዊ መገናኛ መረብ ማዘጋጀቱም ታዉቋል። በተቋሙ የሰልጣኞቹ ቁጥር በእጥፍ ጨምሮ በመጭዉ ዓመት 1000 እንደሚሆኑ ፕሬዚዳንት ኦባማ ቃል መግባታቸዉ ታዉቋል ።
መክብብ ሸዋ
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ