የአፍሪቃ ወጣቶች ቀን
ረቡዕ፣ ጥቅምት 23 2009ማስታወቂያ
የኅብረቱ ባለስልጣናትም በአፍሪቃ ከ400 ሚሊየን የሚበልጠዉ ወጣት ኃይል የነገዋን ክፍለ ዓለም ለመረከብ ዝግጁ መሆን እንደሚገባዉ ያሳሰቡ ሲሆን፤ ዕለቱን ባዘከረዉ ጉባኤ የተገኙት ወጣቶችም፤ የአፍሪቃ የልማት ማዕቀፍ አካል ለመሆን ፈቃደኝነታቸዉን መግለጻቸዉን የኅብረቱ ድረ ገጽ ላይ የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። ከአምስቱ የአፍሪቃ አህጉር አካባቢዎች እና በሌላ ሀገር የሚኖሩ 300 ወጣቶች ትናንት በተከበረዉ የአፍሪቃ ወጣቶች ቀን ላይ ተገኝተዋል። ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ከአዲስ አበባ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ሸዋዬ ለገሠ
አዜብ ታደሰ