1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ዉሕደትና ፈተናዉ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 30 2001

የአፍሪቃ መንግሥት ለመመስረት ማሰብ ባንደኛዉ ምሑር አባባል «ከፈረሱ ፊት ጋሪዉን ማስቀደም ነዉ።»

https://p.dw.com/p/HmKN
የአፍሪቃ ሕብረት ጉባኤምስል AP

የአፍሪቃ ሐገራት የጋራ መንግሥት እንዲያቆሙ አንዳድ የአሐጉሪቱ መሪዎች የሚያደርጉትን ግፊት የተለያዩ አፍሪቃዉያን ምሁራን ተቃወሙት።ባለፈዉ ጥር አዲስ አበባ ላይ ተሰብስበዉ የነበሩት የአፍሪቃ ሐገራት መሪዎች የአፍሪቃ ሕብረት ወደ አፍሪቃ ባለሥልጣን ከፍ ብሎ የተባበሩት የአፍሪቃ መንግሥታት የሚመሰረትበትን ሥልት እንዲያፈላልግ ተስማምተዉ ነበር።ትናንት እዚያዉ አዲስ አበባ ዉስጥ በጉዳዩ ላይ የተነጋገሩት የአፍሪቃ ምሑራን እንዳሉት ግን አሁን ባለዉ የምጣኔ ሐብት እድገትና የፖለቲካ ሁኔታ አንድ የአፍሪቃ መንግሥት ለመመስረት ማሰብ ባንደኛዉ ምሑር አባባል «ከፈረሱ ፊት ጋሪዉን ማስቀደም ነዉ።» ታደሰ እንግዳዉ ተጨማሪ ዘገባ አለዉ።

ታደሰ እንግዳዉ

ነጋሽ መሐመድ