1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ዋንጫ ዝግጅት እና ኢትዮጵያ

ዓርብ፣ ጥር 10 2005

የአፍሪቃ አህጉር የዘንድሮው የእግር ኳስ ዋንጫ ቅድመ-ዝግጅት፣በጀርመናውያን እይታ ምን ይመስላል? ለዋንጫ ዋንኞቹ ተፎካካሪዎች እነማን ይሆኑ? አይቮሪኮስት፣ ዛምቢያ ወይስ ፣ እ ጎ አ የ 2010 የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ፣ እንዲሁም የዘንድሮው

https://p.dw.com/p/17NDE
Afrika Cup 2013 (Logo)

 የአፍሪቃ ዋንጫ አስተናጋጅ ሀገር ደቡብ አፍሪቃ!? ነገ ፣ ቅዳሜ ጥር 11 ቀን 2005  የሚጀመረው ውድድር ፣ የ 16 አገሮች ብሔራዊ ቡድኖች የሚሳተፉበት ነው።

ለነገሩ፤ ውድድሩ በተረኛዋ  ሊቢያ  ነበረ መስተናገድ የነበረበት። ይሁንና አምና በተፈጠረው የእርስ-በርስ ጦርነትና ከዚያም በቀጠለው  አለመረጋጋት ሳቢያ በሌላ ቦታ ቢዘጋጅ  ይሻላል ተብሎ፣  እ ጎ አ ከ 1996 ዓ ም ወዲህ ዕድሉ ዳግመኛ   ለደቡብ አፍሪቃ ሊሰጥ ችሏል።

Nigeria's attacker Victor Anichebe (C) struggles for possession of ball with Ethiopian skipper Samson Gebreegziabher (R) and Abebaw Bune during the African Cup of Nations qualifying match between the two countries in Abuja Sunday, March 27, 2011. Nigeria defeated Ethiopia 4 - 0. AFP PHOTO/PIUS UTOMI EKPEI (Photo credit should read PIUS UTOMI EKPEI/AFP/Getty Images)
የኢትዮጵያ ቡድን ከደቡብ አፍሪቃዉ ጋርምስል Getty Images/AFP

«ውድድሩን የማዘጋጀት ዕድል ለተሰጣት ለደቡብ አፍሪቃ  ይህ ክብር ነው። ከ 2010 የዓለም ዋንጫ ወዲህ፤ የዘንድሮው የአፍሪቃ ዋንጫ ውድድር በዚያ እንዲስተናገድ ማድረጉ ብልህነት የተንጸባረቀበት ውሳኔ ነው። አገሪቱ፤ በመሠረተ ልማቱም ሆነ ፤ የተሳካ ውድድር ማዘጋጀት የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ታሟላለችና!»

Max Grünewald በደቡብ አፍሪቃ አንደኛ ምድብ ከሚገኙት የአግር ኳስ ክለቦች፣ አያክስ ካፕሽታት ቡድን አሠልጣኝ ናቸው።

ጥር 11 የመክፈቻውና ፣   እሁድ የካቲት 3,2005 ዓ ም የፍጻሜው ግጥሚያ የሚካሄደው ጆሃንስበርግ ውስጥ በ «ሳከር ሲቲ ስቴዲዬም »   ነው። የድርባኑ ሞሰስ -ማብሂዳ ስቴዲየማና ሌሎችም ለግጥሚያ ተመድበዋል።  በ 2012 ጋቡን በተካሄደው የፍጻሜ ግጥሚያ፣ ሳይታሰብ፤ ዛምቢያ አይቮሪኮስትን አሸንፋ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ የዋንጫ ባለቤት መሆኗ አይዘነጋም። Max Grünewald  አሁንም 2 ቱ ቡድኖች ጥሩ ዕድል እንዳላቸው ያምናሉ።

12 Feb 2012Zambia's goalkeeper Kennedy Mweene (L) kisses the trophy during the award ceremony following their African Cup of Nations (CAN 2012) match against Ivory Coast on February 11, 2012 at the stade de l'Am... Erfahren Sie mehrVon: FRANCK FIFEKollektion: AFP
ሰኞ ከኢትዮጵያ ቡድን ጋር የሚገጥመዉ-የዛምቢያ ቡድንምስል gettyimages/AFP

«አይቮሪኮስት በኮከብ የፊት አጥቂ ድሮግባ እርዳታ እንዳለፈው ጊዜ፤ ቡድኑ በ ፍጹም ቅጣት ምት ሳይሸነፍ ፣ አሁን ውጤት ለማስመዝገብ መሰለፉ አይቀርም። ናይጀሪያን የመሳሰሉትንም በቀላሉ መገመት የሚቻል አይደለም። »

ደቡብ አፍሪቃ በምድብ ሀ  ከሞሮኮ አንጎላና አስገራሚ ከተባለችው ካፑቨርድ ጋር ትጋጠማለች። ደሴቲዩ ካፑቨርድ፤ በማጣሪያ ግጥሚያ  ካሜሩንን አሸንፋ ያስቀረች መሆኗ የሚዘነጋ አይደለም። ጋና በምድብ  ለ  ከማሊ ፣ ኒዠርና ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ጋር ይሆናል ውድድሯ! የዋንጫ ባለቤት ዛምቢያ፤ በ3ኛ ምድብ ከናይጀሪያ ቡርኪና ፋሶና ኢትዮጵያ ጋር ናት። በምድብ  መ  አልጀሪያ ቱኒሲያ፤ አይቮሪኮስትና ቶጎ ተጋጣሚዎች ናቸው።

አንዳንድ በከፍተኛ ደረጃ የታወቁ አፍሪቃውያን  እግር ኳስ ተጫዋቾች፣ አገሮቻቸውን ወክለው ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ከመገኘት ይልቅ፣  አውሮፓ ውስጥ ለክለቦቻቸው መሰለፉን ቢመርጡም፤ ግሩዑነቫልድ እንደሚሉት፣ በዛ ያሉ ሌሎች ተጫዋቾች ብቅ-ብቅ ማለታቸው አይቀሬ ነው።ደቡብ አፍሪቃ፤ የዓለምን ዋንጫ በተሳካ ሁኔታ ካስተናገደች ወዲህ፤ የቀድሞው የብሔራዊ ቡድኗ ተጫዋች ዴቪድ ኒያቲ እንደሚለው፣ አሁንም መሰናዶዋ እንደገና የሠመረ እንደሚሆን አያጠራጥርም።

26 Mrz 2011JOHANNESBURG, SOUTH AFRICA - MARCH 26: South Africa starting team poses during the 2012 Africa Cup of Nations Qualifier match between South Africa and Egypt at Coca Cola Park on March 26, 2011 in Joh... Erfahren Sie mehrVon: Gallo ImagesKollektion: Getty Images Sport
አስተናጋጁ-የደቡብ አፍሪቃ ቡድንምስል gettyimages

«ይህ ፣ ለኛ ፣  ለቱሪዝም ገበያና ለእግር ኳስ አፍቃሪው ህዝብም  ትልቅ ዕድል ነው። ዓለም ፣ አንዲት አዳጊ ሀገር ምን ማከናወን እንደምትችል ዓለም አቀፉን የእስፖርት ማኅበረሰብም  ማስተናገድ የምትችል መሆኗን ያይላታል፣ እኛም የኩራት ስሜት ያድርብናል። »

የ 43 ዓመቱ ኒያቲ ይህ ውድድር ፣ ለክፍለ-ዓለሙ በመላ ማለፊያ  ሥም እንደሚያሰጥም ተስፋውን ገልጾአል።

«ውድድሩ፤ አፍሪቃ በአስፖርት ምን እንደሚመስል ያሳያል። የተነቃቃ ዐቢይ የእስፖርት ኃይል  መሆኑንም ያሥመሰክርበታል። የአፍሪቃ ዋንጫ  ውድድር ፤ አንድ ጊዜ በዓለም ዋንጫ ደረጃ ሊገኝ እንደሚችልም ያለንን ተስፋ ሊያለመልም ይችላል።»

Nigerian striker Victor Moses jumps on goal scorer Mikel Obi (L), Umar Zango (C) and Amed Musa celebrating a Nigerian fourth goal against Liberia during the 2013 African Cup of Nations second leg qualifying match between the two countries at Calabar October 13, 2012. Nigeria defeated Liberia 6 - 1 to qualify for the tournament to be held in South Africa next year. AFP PHOTO/PIUS UTOMI EKPEI . (Photo credit should read PIUS UTOMI EKPEI/AFP/GettyImages)
የናጄሪያ ቡድንም ከኢትዮጵያ ጋር ይገጥማልምስል Getty Images/AFP

የአፍሪቃ ዋንቻ ውድድር አሸናፊ ብራዚል ውስጥ ለሚካሄደው የ 2013 የዓለም ኮንፈዴሬሽን ዋንጫ ውድድር በቀጥታ ያልፋል። የአግር ኳስ አፍቃሪ ቤሪ ፣ በተለይ በዚያች ሀገር እግር ኳስ ካለው እጅግ ተወዳጅነት ጋር፣  ብዙ እንግዶች እንደሚገኙ ተስፋ ያደረጋል።

«ለማንም የምሰጠው ምክር፤ በደቡብ አፍሪቃ የሚካሄደውን የእግር ር ኳስ ጨዋታ እንዲመለከት ነው። አወንታዊ ኃይልና መንፈስ  ነው የሚያጎናጽፈው። በደቡብ አፍሪቃ እግር ኳስ ህይወት አዳሽ  መሆኑንም መገንዘብ ያስችላል።»

                              -------------------------------------------

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ነገ-በይፋ በሚጀመረዉ ሃያ-ዘጠነኛዉ የአፍሪቃ የእግር ኳስ የዋንጫ ግጥሚያ ላይ ለመካፈል ዛሬ ጁሐንስበርግ ይገባል።ምናልባትም ስትዲዮ ከመጣሁ በሕዋላ ገብቶም ይሆናል።ደቡብ አፍሪቃ የሚኖሩና ደቡብ አፍሪቃ የገቡ በርካታ ኢትዮጵያዉያን ቡድኑን ለመቀበል ከማለዳዉ ጀምረዉ የጁሐንስበርጉን አዉሮፕላን ማረፊያ አጨናንቀዉት ነዉ የዋሉት። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በታላቁ የአፍሪቃ የእግር ኳስ ግጥሚያ ሲካፈል ከሰላሳ ዓመት ወዲሕ ያሁኑ የመጀመሪያዉ ነዉ-የሚሆነዉ።ዉድድሩን ለመከታተል ከፓሪስ ወደ ጁሐንስበርግ የሔደችዉ ዘጋቢያችን ሐይማኖት ጥሩነት እንዳለችዉ ታላቁን ግጥሚያ የምታስናግደዉ ደቡብ አፍሪቃ በጣሙን ጀሐንስ በርግ ግን ገና የምታንቀላፈ ነዉ-የምትመስለዉ።ሐይማኖትን ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት በሥልክ አነጋግሬያት ነበር።

ተክሌ የኋላ

ሐይማኖት ዓለሙ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ