1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ የመሬት ቅርምትና ችግሩ

ረቡዕ፣ ሰኔ 8 2003

ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪቃ የተስፋፋው ሰፋፊ መሬትን በተለያየ መንገድ ለውጭ ባለሃብቶች መስጠት ለሃገራቱ ምጣኔ ሃብት እድገት አንዳችም ፋይዳ እንደሌለው ተገለፀ ።

https://p.dw.com/p/RTmi
ምስል picture-alliance / dpa

ዩናይትድ ስቴትስ የሚገኘው ኦክላንድ ኢንስቲትዩት የተባለው ተቋም በቅርቡ ያወጣው ጥናታዊ ዘገባ መሬት ለውጭ ባለሀብቶች መሰጠቱ ገበሬዎችን እንደሚያፈናቅል እና የምግብ ዋስትናን እንደሚያሳጣም አስታውቋል ። በዘገባው በሃገራቱ የመሬት አሰጣጡም ለሙስና የተጋለጠ መሆኑ ተጠቁሟል ። በአሜሪካን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ስለ ዘገባው ለዶቼቬለ በሰጠው መለስ ዘጋባው ውስጥ የተካተቱት ድምዳሜዎች ኢትዮጵያን አይመለከቱም ብሏል ።

አበበ ፈለቀ

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ