1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ የሰብዓዊ መብት ቀን

ረቡዕ፣ ጥቅምት 10 2008

የሕብረቱ የፖለቲካ ኮሚሽነር አይሻ አብዱላሂ ባሰሙት ንግግር ከአፍሪቃ የሴቶችን መብት በማስጠበቅ ሩዋንዳን አወድሰዋል። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቶቻቸው የተወከሉ ሴቶች ቁጥር ከፍተኛ የሆነባቸውን አንዳንድ የአፍሪቃ ሃገራትም በምሳሌነት አንስተዋል።

https://p.dw.com/p/1GsEu
Bildergalerie Millionäre Afrika - AU Conference Center
ምስል picture-alliance/Zuma Press

[No title]

በአፍሪቃ የሰብዓዊ መብት አያያዝ በሰፊው የሚያነጋግር ርዕስ ከሆነ ከርሟል ።ያም ሆኖ የአፍሪቃ ሕብረት የክፍለ ዓለሙን የሰብዓዊ መብት ቀን በሕብረቱ አዳራሽ ዛሬ አስቧል። በዚሁ ሥነ-ስርዓት ላይ የሕብረቱ የፖለቲካ ኮሚሽነር አይሻ አብዱላሂ ባሰሙት ንግግር ከአፍሪቃ የሴቶችን መብት በማስጠበቅ ሩዋንዳን አወድሰዋል። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቶቻቸው የተወከሉ ሴቶች ቁጥር ከፍተኛ የሆነባቸውን አንዳንድ የአፍሪቃ ሃገራትም በምሳሌነት አንስተዋል። የሴቶችን መብት ማስከበር ወደፊትም ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባው መሠረታዊ ጉዳይ መሆኑን ባለሥልጣንዋ ተናግረዋል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ