የአፍሪቃ የተፈጥሮ ሐብት ችግርና የካሳ ጥያቄ
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 3 2002ማስታወቂያ
የአፍሪቃ ሕብረትና የተፈጥሮ ሐብት
አፍሪቃ ዉስጥ ለደረሰዉ የአየር ንብረት መዛባት ተጠያቂዎቹ የበለፀጉት ሐገራት እንደሆኑ የአፍሪቃ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳት አስታወቁ።የሕብረቱ ፕሬዝዳት ዣን ፒንግ ዋጋዱጉ-ቡርኪናፋሶ ዉስጥ በተደረገ ጉባኤ ላይ እንደተናገሩት የበለፀጉት ሐገራት በአፍሪቃ ላደረሱት ጥፋት ካሳ መክፈል አለባቸዉ። የአፍሪቃ ሕብረት በክፍለ-አለሚቱ ለደረሰዉ የአየር ንብረት ብክለት የበለፅጉት ሐገራት 65 ቢሊዮን ዶላር ካሳ እንዲከፍሉ ከዚሕ ቀደም ጠይቆ ነበር።ፒንግ ጥያቄዉን በድጋሚ አሰምተዋል።ጌታቸዉ ተድላ ዝር ዝሩን አጠናቅሮታል።
Getachew Tedla
Negash Mohammed