1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪካና ህንድ ምጣኔ ሀብታዊ ግንኙነት

ረቡዕ፣ ግንቦት 17 2003

በህንድና በአፍሪካ መሀል ያለው የንግድ ግንኙነት እየተጠናከረ መምጣቱ በታየበት በዚህ ጉባዔ ህንድ ለአፍሪካ የ5ቢሊዮን ዶላር ብድር በሚቀጥሉት 3ዓመታት ውስጥ ለመስጠት ቃል ገብታለች።

https://p.dw.com/p/RQ2c
ምስል picture-alliance/ dpa

ካለፈው ዓርብ ጀምሮ ሁለተኛው የአፍሪካና ህንድ ምጣኔ ሀብታዊ ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። የሁለቱ ወገኖች ግንኙነት ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች ላይ ብቻ ያተኮረ ሳይሆን በፖለቲካዊ አቅጣጫም አዲስ የግንኙነት ምዕራፍ ለመክፈት ያለመ እንደሆነ ተገልጿል። በተለይ ህንድ በመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ ወንበር ለማግኘት የአፍሪካን ድጋፍ በእጅጉ ትሻለች። መሳይ መኮንን በህንድና አፍሪካ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና የንግድ ግንኙነት ዙሪያ የእንግሊዘኛውን ፎርቹን ጋዜጣ መራሄ አዘጋጅ ታምራት ገብረጊዮርጊስን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ አሰናድቷል።

ከእስያው አህጉር በኢኮኖሚ ሶስተኛዋ ትልቋ ሀገር ናት ህንድ። ቻይና፤ ሩሲያ፤ ብራዚልና ደቡብ አፍሪካ በሚገኙበት 5ቱ በኢኮኖሚው ግስጋሴ ላይ ካሉት ሀገራትም አንዷ ናት። በአፍሪካ ቻይናን በመከተል ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ ያለው የንግድ ሽርክና አላት። በሁለተኛው የአፍሪካ ህንድ የምጣኔ ሀብታዊ ጉባዔ ላይ እንደተገለጸው በህንድና በአፍሪካ ሀገራት መሀል ያለው የንግድ ግንኙነት 46ቢሊዮን ዶላር ደርሷል። በእርግጥ ህንድ አፍሪካን በእጅጉ እንደምትፈልጋት ነው ጠቅላይ ሚኒስትሯ ማንሞሀን ሲንግ አዲስ አበባ ላይ በተደረጉው ጎባዔ ላይ በይፋ የገለጹት። የፎርቹን የእንግሊዘኛ ጋዜጣ መራሄ አዘጋጅ ታምራት ገብረጊዮርጊስ እንደሚሉት እንደህንድ ለመሳሰሉ በኢኮኖሚው ግስጋሴ ላይ ላሉ ሀገራት አፍሪካ የተመቸች ቦታ ናት።

ህንድ ወደ አፍሪካ ስታነጣጥር በእርግጥ ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቱን ብቻ አቅዳ አይደለም። ፖለቲካዊ ስሌትንም በጎኑ ይዛለች። ጋዜጠኛ ታምራት

አፍሪካ በኢኮኖሚው ግስጋሴ ላይ ካሉት ሀገራት በተለይም ከቻይናና ከህንድ ጋር ያላት ግንኙነት ባለፉት አስር ዓመታት ውስጥ በከፍተኛ መጠን ጨምሯል። ቻይና በአሁኑ ጊዜ የ107 ቢሊዮን ዶላር የንግድ ሽርክና አላት ከአፍሪካ ጋር። ይህም ከህንድ ጋር ካላት ሲነጻጸር ከዕጥፍ በላይ ይልቃል። በእርግጥ ህንድ የቻይናን ያህል ከፍተኛ የሆነ መዋዕለ ነዋይ አፍሪካ ላይ አላፈሰሰችም። የፍሮቹን ጋዜጣ መራሄ አዘጋጅ ታምራት ገብረ ጊዮርጊስ ቻይና ከህንድ የላቀ ድርሻ መያዝዋ አያስገርምም ይላሉ።

በእርግጥ የኢትዮድያና ህንድ ኢኮኖሚያዊ ግንኑነትም አድጓል። በአሁኑ ጊዜ በኢትዮዽያ ያለው የህንድ መዋዕለ ነዋይ ፍሰት 4.5ቢሊዮን ዶላር ደርሷል።

መሳይ መኮንን

ሸዋዬ ለገሰ

አርያም ተክሌ