1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢህአዴግ ዓመታዊ ግምገማ

Merga Yonas Bulaማክሰኞ፣ ነሐሴ 17 2008

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር /ኢህአዴግ/ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባለፈዉ ሳምንት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ያለፉትን አስራ አምስት ዓመታት የለውጥ ጉዞ ገምግሞ መግለጫ አዉጥተዋል።

https://p.dw.com/p/1Jnpl
Karte Äthiopien englisch

[No title]

በዚሁ ግምገማ የመንግስት ተልዕኮ «ህዝብን ማገልገልና በዚህ ቅኝት መንቀሳቀስ እንጂ የግል መጠቀሚያ» እንዳልሆነ ጠቅሶ «ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱን» ይፈታተናሉ ያላቸዉን «የውጭም ሆነ የውስጥ ፅንፈኛ ፀረ ሰላምና ፀረ ልማት ኃይሎች---ሁከትና ትርምስን ለማስፋፋት የሚያደርጉትን ጥረት በፅናት» ይመክታል ይላል። ቀጥሎም በአገሪቱ ብሄር ብሄረሰብ መካከል ያለዉን ግኑኝነት ለማሻከር «አስነዋሪ የዘረኝነት ፕሮፓጋንዳ» የሚያራምዱትን እንደምታገል ይጠቅሳል።


በዝህም ግምገማ ኢህአዴግ የስረዓቱ አደጋ ናቸዉ ላላቸዉን እና የህዝብቡ ጥያቄ አሌበት ያለዉን «የክራይ ሰብሳብነት አመለካከት፣ ድሞክራስና ሰባዊ መብት አያያዝ እንድሁም የጠባብነትና የትምክተኝነት አመለካከት» መፍቴ መስጠት መፈለጉን ጋዝጤኛና የየህግ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሶሎሞን ጎሹ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል።

ኢህአዴግ የ15 ዓመት ጉዞዉን መለስ ብሎn ተመልክቶዋል ያለበትን ግምገማ የሰማያዊ ፓርት የህግ ጉዳይ አላፍ የሆኑት አቶ አድሱ ግታኔ ከበፍቱ የተለየ ሆኖ እንዳላገኙት ለዶቼ ቬሌ ገልጸዋል።

በፌስቡክ ደህረ ገፃችን ላይም አስተያየት ከሰጡን ዉስጥ hንግስት በፖሊስ ደረጃ እየሰራዉ ነዉ ያሉትን ስህተት ማራም አለበት ብለዋል።

መርጋ ዮናስ

አሪያም ተክሌ