1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢሕአዴግ ውሳኔ ምን ይፈይድ ይሆን?

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 27 2010

የአፍሪቃ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ሙሳ ፋኪ ማሕማት የጠቅላይ ምኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ መንግሥት ለፖለቲካ ፓርቲ አባላት እና ሌሎች ግለሰቦች ይቅርታ ለማድረግ አሊያም ክሳቸውን ለማንሳት መወሰኑን አድንቀዋል።

https://p.dw.com/p/2qPtb
Äthiopien PK Ministerpräsident Hailemariam Desalegn
ምስል EBC

የኢሕአዴግ ውሳኔ ፋይዳ

የኢህአዴግ ውሳኔ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን ጨምሮ ከዓለም አቀፍ ተቋማት በጎ ተቀባይነት አግኝቷል። የአፍሪቃ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ሙሳ ፋኪ ማሕማት የጠቅላይ ምኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ መንግሥት ለፖለቲካ ፓርቲ አባላት እና ሌሎች ግለሰቦች ይቅርታ ለማድረግ አሊያም ክሳቸውን ለማንሳት መወሰኑን አድንቀዋል። የኢሕአዴግ ውሳኔዎች የኢትዮጵያን መረጋጋት እንደሚያጠናክሩ ማሕማት እምነታቸውን ገልጸዋል።

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ሒውማን ራይትስ ዎች በበኩሉ ውሳኔው መቼ እና እንዴት ተግባራዊ እንደሚሆን ባይገለጥም በአገሪቱ ተንሰራፍቷል ያለውን ፖለቲካዊ ጭቆናና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለማብቃት ሁነኛ እርምጃ ነው ብሏል። ሒውማን ራይትስ ዎች በመግለጫው ያነሳቸው መሠረታዊ ጥያቄዎች አሉ። ከዚህ በኋላ በእርግጥ ኢትዮጵያውያን እታሰራለሁ፣ ፖለቲካዊ ክስ ይገጥመኛል፣ የሚል ሥጋት ሳይጫናቸው ተቃውሟቸውን በሰላማዊ መንገድ ማቅረብ ይችሉ ይሆን? ሲል ጠይቋል። የለንደኑ ወኪላችን ድልነሳ ጌታነሕ ደግሞ የኢሕአዴግ ውሳኔ በሚኖረው ፋይዳ ላይ ኤማ ጎርደንን አነጋግሯቸዋል። ኤማ ጎርደን የአፍሪቃ የፖለቲካ ተንታኝ ናቸው።  

ድልነሳ ጌታነሕ

እሸቴ በቀለ

ሸዋዬ ለገሠ