1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢሕአዴግ ደጋፊዎች ሠልፍ በአዲስ አበባ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 17 2002

ኢትዮጵያ ዉስጥ ባለፈዉ እሁድ በተደረገዉ ምርጫ የሐገሪቱ ገዢ ፓርቲ ኢሕአዴግ አሸነፈ መባሉ ያስደሰታቸዉ የአዲስ አበባ ነዋሪ የኢሕአዴግ ደጋፊዎች ዛሬ በሰልፍ አደባባይ ወጥተዉ ነዉ-ያረፈዱት።

https://p.dw.com/p/NWmj
ምስል DW

ሠልፈኞቹ በምርጫዉ ዉጤት መደሰታቸዉን ከመግለጣቸዉም ባሻገር የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችንና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማትን አዉግዘዋል።ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ለሰልፈኛዉ ባደረጉት ንግግር የአዲስ አበባ ሕዝብ ፍትሐዊ ብያኔ እንደሚያዉቅ በሰጠዉ ድምፅ አረጋግጧል ብለዋል።ታደሰ እንግዳዉ ሠልፉን ተከታትሎት ነበር።

ታደሰ እንግዳዉ

ነጋሽ መሀመድ

አርያም ተክሌ