1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢራኑ ፕሬዝደንት በአዉሮጳ

ዓርብ፣ ጥር 20 2008

ኢራን ከምዕራባዉያን መንግሥታት ጋር ባደረገችዉ ስምምነት መሠረት በኑኬለር መርሐ-ግብሯ ሰበብ የተጣለባት ማዕቀብ በመነሳቱ ከምዕራባዉያን ጋር አቋርጠዉ የነበረዉን የንግድና የምርት ልዉዉጥን እንዳዲስ እየጀመረች ነዉ። የማዕቀቡ መነሳት ከኢራን ጋር ለሚሠሩ የአዉሮጳ ኩባንዮችም ሠፊ ገበያ እና የሥራ እድል ፈጥሯል።

https://p.dw.com/p/1Hluj
ምስል Reuters/C. Platiau

[No title]

የኢራን ፕሬዝደንት ሐሰን ሩሐኒ የመሩት የሐገሪቱ የመልዕክተኞች ቡድን በኢጣሊያና በፈረንሳይ ባደረገዉ ጉብኝት ከሁለቱ መንግሥታት ባለሥልጣናትና የኩባንያ ሐላፊዎች ጋር በብዙ ቢሊዮን ዩሮ የሚቆጠር የንግድና የልማት ትብብር ተፈራርሟል።ኢራን ከምዕራባዉያን መንግሥታት ጋር ባደረገችዉ ሠምምነት መሠረት በኑኬለር መርሐ-ግብሯ ሰበብ የተጣለባት ማዕቀብ በመነሳቱ ከምዕራባዉያን ጋር አቋርጠዉ የነበረዉን የንግድና የምርት ልዉዉጥን እንዳዲስ እየጀመረች ነዉ። የማዕቀቡ መነሳት ከኢራን ጋር ለሚሠሩ የአዉሮጳ ኩባንዮችም ሠፊ ገበያ እና የሥራ እድል ፈጥሯል። የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዝርዝር ዘገባ አለዉ።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ