1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢራን ምርጫ ውጤት ያስከተለው ውዝግብ ና ግጭት

ማክሰኞ፣ ሰኔ 9 2001

ባለፈው አርቡ የኢራን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የኢራኑ ፕሬዝዳንት ማህሙድ አህመዲነጃድ ማሸነፋችው ይፋ ከሆነበት ከቅዳሜ አንስቶ ኢራን በአመፅ እየተናወጠች ነው ።

https://p.dw.com/p/IBqb
ሙሳቪ ንግግር ሲያደርጉምስል DW

ድምፅ ቆጠራው ተጭበርብሯል የሚሉት የዕጩ ፕሬዝዳንት ሚርሆሴን ሙሳቪ ደጋፊዎች ተቃውሞአቸውን በመላ ኢራን በተለያየ መንገድ እየገለፁ ነው ። በዋና ከተማይቱ በቴህራን በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ የሙሳቪ ደጋፊዎች ትናንት አደባባይ በመውጣት አመፅ የተቀላቀለበት ተቃውሞ አካሂደዋል ። ያለ መንግስት ፈቃድ በተካሄደውና ዕጩ ተወዳዳሪ ሙሳቪ በተገኙበት በዚሁ የተቃውሞ ሰልፍ መንስኤም የሰባት ሰዎች ህይወት ጠፍቷል ። መንግስት የአመፁ ቆስቋሽ ናቸው ያላቸውን ሰዎች እያሰረ ነው ።

ሂሩት መለሰ/አርያም ተክሌ