1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢራን የኒኩሊየር መርሃግብር ድርድር

ረቡዕ፣ መጋቢት 23 2007

እስከትናንት የመጨረሻ ቀነ ገደብ ተሰጥቶት የነበረዉ የኢራን የኒኩሊየር መርሃግብር ድርድር ዛሬም እንደገና መቀጠሉ እየተነገረ ነዉ። ዘገባዎች እንደሚሉት ከስድስቱ ሃገራት የሶስቱ ተደራዳሪዎች አልተገኙም።

https://p.dw.com/p/1F1Cy
Schweiz Lausanne Atomverhandlung Delegationen
ምስል Getty Images/AFP/F. Coffrini

ላለፉት ስድስት ቀናት ሲካሄድ የቆየዉ ድርድር ካለዉጤት እንዳይበተን ከፍተኛ ትኩረት የሰጡት የዩናይትድ ስቴትስ፣ ብሪታንያ እና ጀርመን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ዛሬም ከኢራኑ አቻቸዉ ሞሀመድ ጃቫ ዛሪፍ ጋ በስዊዘርላንዷ ሎዛን ከተማ ንግግር መቀጠላቸዉ ተዘግቧል። የሩሲያ፤ ቻይና እና ፈረንሳይ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ግን ትናንት ማምሻዉን ወደየሀገራቸዉ መመለሳቸዉ ተሰምቷል። ትናንት ዉይይቱ ሲቋረጥም የኢራኑ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለአብዛኞቹ ችግሮች መፍትሄ መገኘቱን ተናግረዋል። የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክልም በድርድሩ አግባቢ ነጥብ ላይ ይደረሳል የሚል ተስፋቸዉን ገልጸዋል። የኢራንን የአቶም መርሃግብር በስጋት የምትከታተለዉ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በበኩላቸዉ ድርድሩ ትርጉም ያለዉ ስምምነት እንዲያስገኝ አጥብቀዉ እያሳሰቡ ነዉ። ስለቀጠለዉ የኢራን ድርድር ብራስልስ የሚገኘዉ ዘጋቢችን ገበያዉ ንጉሤን አንዳንድ ነጥቦች በማንሳት ቀደም ብዬ በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ