1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያና ኤርትራ ዲፕሎማቶች ክርክር

ሰኞ፣ ሰኔ 13 2008

የሁለቱ ሃገራት ዲፕሎማቶች ባካሄዱት በዚሁ ክርክር የመንግሥቶቻቸውን እርምጃ ትክክለኛነት ለማስረዳት ከመጣራቸው ውጭ መልሳቸው በእውነተኛው ችግር እና መፍትሄው ላይ ያተኮረ አልነበረም ሲሉ አስተያየት ሰጭዎች ተናግረዋል ።

https://p.dw.com/p/1JABw
Karte Eritrea Äthiopien
ምስል AP Graphics/DW

[No title]

በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል በድንበር ግጭቱ መንስኤ የሚካሄደው የቃላት ጦርነት ባለፈው ሳምንት ተካሮ ነበር የቀጠለው። በሳምንቱ መጨረሻም በኬንያ የኢትዮጲያ አምባሳደርና በኬንያ የኤርትራ አምባሳደር ኬ.ቲ.ኤን በተባለው የኬንያ ቴሌቪዝን ላይ ያካሄዱት ጭቅጭቅ ያመዘነበት ክርክር ላይም ይኽው ተንፀባርቋል ።የሁለቱ ሃገራት ዲፕሎማቶች ባካሄዱት በዚሁ ክርክር የመንግሥቶቻቸውን እርምጃ ትክክለኛነት ለማስረዳት ከመጣራቸው ውጭ እውነተኛው ችግር እና መፍትሄው ላይ ያተኮረ አልነበረም ሲሉ አስተያየት ሰጭዎች ተናግረዋል ። በአነጋጋሪው የሁለቱ ዲፕሎማቶች ክርክር ላይ ስለተሰጡት አስተያየቶች የናይሮቢውን ወኪላችንን ፋሲል ግርማን በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።

ፋሲል ግርማ

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ