1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያና የእስራኤል የትብብር ምክክር

ሐሙስ፣ ጳጉሜን 5 2007

የኢትዮጵያ እና የእስራኤል የንግድ ልውውጥ መጠን ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት ከነበረው ዘንድሮ ከእጥፍ በላይ ማደጉ ተገልጿል። በዚሁ የኢትዮጵያና የእስራኤል የትብብር ምክክር ላይ እንደተገለፀው ኢትዮጵያ ውስጥ በግብርናው መስክ የተሰማሩ በርካታ የእስራኤል ኩባንያዎች አሉ።

https://p.dw.com/p/1GUNR
Äthiopien Israel Ethio-Israel New Cooperation Wondirad Mandefro
ምስል DW/G. Tedla

[No title]

ኢትዮጵያና እስራኤል በግብርናም ሆነ በሌሎች የንግድ ዘርፎች ትብብራቸውን ለማጠናከር የሚያስችል ምክክር አካሄዱ ። በሸራተን ሆቴል በተካሄደው በዚሁ ምክክር ላይ የኢትዮጵያ የግብርና ሚኒስቴር ኃላፊዎች፣ ታዋቂ የእሥራኤል ኩባንያዎች ተጠሪዎች እንዲሁም በኢትዮጵያ የእሥራኤል አምባሳደር ተገኝተዋል። የሁለቱ ሃገራት የንግድ ልውውጥ መጠን ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት ከነበረው ዘንድሮ ከእጥፍ በላይ ማደጉ ተገልጿል። በዚሁ የትብብር ምክክር ላይ እንደተገለፀው ኢትዮጵያ ውስጥ በግብርናው መስክ የተሰማሩ በርካታ የእስራኤል ኩባንያዎች አሉ። የምክክሩን ሂደት የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ አለው ።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

አዜብ ታደሰ