1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያና የደቡብ ኮርያ ግንኙነት

ማክሰኞ፣ ግንቦት 23 2008

ባለፈዉ ሳምንት የምስራቅ አፍሪቃ ጉብኝታቸዉን ከኢትዮጵያ የጀመሩት የደቡብ ኮርያ ፕሬዚዳንት ፓርክ ጌዩን ሄ አፍሪቃ ሰሜን ኮርያን ከኒኩልየር ነፃ ለማድረግ በሚደረገዉ ጥረት ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጎን እንድትቆም መጠየቃቸዉ ይታወቃል። ፕሬዚዳንቷ ይህን የተናገሩት በአፍሪቃ ኅብረት አዳራሽ ተገኝተዉ ባደረጉት ንግግር ነበር።

https://p.dw.com/p/1Ixho
Äthiopien Addis Abeba Besuch Park Geun-hye
የደቡብ ኮርያ ፕሬዚዳንት ፓርክ ጌዩን ሄ አዲስ አበባን በጎበኙበት ወቅት በአፍሪቃ ኅብረት የተገኙት ኮርያዉያን በከፊልምስል DW/G. Tedla

[No title]


ፕሬዚዳንት ፓርክ መንግሥታቸዉ ጥቃትንና ጽንፈኝነትን ለመታገል ከአፍሪቃ ሃገራት ጋር እንደሚሰራም ገልፀዋል። ፕሬዚዳንት ፓርክ ደቡብ ኮርያ « የአፍሪቃ ወዳጅ » እንድትሆን እንደሚሰሩና የልማት ግንኙነትን በተመለከተ በንግድ በትምህርት እንዲሁም ባህላዊ ትስስር የአፍሪካ-ደቡብ ኮሪያን ግንኙነት ያሳድጋል የሚል ተስፋ የጣሉበትን ንድፍም ማቅረባቸዉ ይታወቃል። የረጅም ጊዜ ታሪክ ያላቸዉ ደቡብ ኮርያና ኢትዮጵያ በተለይ በፕሬዚዳንትዋ ጉብኝት ይበልጥ መጠናከሩ ነዉ የተመለከተዉ። ከ 65 ዓመት በፊት በኮርያ በነበረዉ ጦርነት ኢትዮጵያዉያን አርበኞች በመንግስታቱ ድርጅት ጦር ኃይል ሥር ተሳታፊ መሆናቸዉ ይታወቃል። የደቡብ ኮርያ መንግሥት ዛሬ ከ 65 ዓመት በኋላ እነዚህን አባት ጡረተኞች እየረዳ መሆኑም ነዉ የተነገረዉ። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን የኮርያ ዘማች አርበኞች ማኅበር ፕሬዚዳንትን አነጋግሮ ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ


አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ