1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሰማያዊ ፓርቲ ለጠፋው የሰው ሕይወት ተጠያቂ ግለሰቦች ለፍርድ ይቅረቡ ብሏል

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 10 2010

የሰማያዊ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እንደሚሉት ለጠፋው የሰው ሕይወት እና ለወደመው ንብረት ተጠያቂ የሆኑ ግለሰቦች "እንደለመዱት በግምገማ" ሊታለፉ አይገባም። የፓርቲው አመራሮች "አሁንም ቢሆን አልረፈደም።" እያሉ ነው።

https://p.dw.com/p/2perK
Äthiopien Addis Abeba Pressekonferenz Parteien
ምስል DW/G. T. Hailegiorgis

ሰማያዊ ፓርቲ ለጠፋው የሰው ሕይወት ተጠያቂ ግለሰቦች ለፍርድ ይቅረቡ ብሏል

ውስጣዊ ሽኩቻ ያየለበት፤ ተቃውሞ እና ኹከት የጠናበት ገዢው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር የሥራ አስፈፃሚ ስብሰባ ተቀምጧል። በምን ላይ መከረ? ምን ውሳኔ አስተላለፈ? የገጠመውን ቀውስስ እንዴት ሊፈታው አቅዶ ይሆን? የመንግሥት ደጋፊዎች በማኅበራዊ ድረ-ገፆች ከሚያሰራጩት ተባራሪ ወሬ በቀር የሚታወቅ ነገር የለም።
የተማሪ ሕይወት በጠፋባቸው የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ያረበበው ውጥረትም አልረገበም። በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልል አዋሳኝ ወረዳዎች ግጭት እና ኹከት በርትቷል። ሰዎች ይገደላሉ፣ ይፈናቃላሉ፣ የመኖሪያ ቤታቸውም ይቃጠል ይዟል። የሰማያዊ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እንደሚሉት ለጠፋው የሰው ሕይወት እና ለወደመው ንብረት ተጠያቂ የሆኑ ግለሰቦች "እንደለመዱት በግምገማ" ሊታለፉ አይገባም። የፓርቲው አመራሮች የኢትዮጵያን ቀውስ ለመፍታት "አሁንም ቢሆን አልረፈደም።" እያሉ ነው። የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የተቃዋሚው የሰማያዊ ፓርቲን የጋዜጣዊ መግለጫ ተከታትሎት ነበር።
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር 
እሸቴ በቀለ
ሸዋዬ ለገሠ