1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያዊው ተጠርጣሪ የሕገ ወጥ ሰው አዘዋዋሪ ጉዳይ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 21 2007

ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ ከአፍሪቃ ወደ አውሮጳ ለመግባት የሚሞክሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ያሰቡት ቦታ ሳይደርሱ በምድረ በዳው ሀሩር እና በሜድትሬንያን ባህር ማዕበል ሰበብ ወይም ከሚገባቸው በላይ ተሳፋሪዎችን የጫኑ

https://p.dw.com/p/1G6X6
Flüchtlingsaufnahmelager der Caritas in Palermo, Italien
ምስል DW/B. Riegert

[No title]

 

የማያስተማምኑ ጀልባዎቻቸው እየሰመጡ የትም ወድቀው የሚቀሩበት ድርጊት አሳዛኝ ክስተት መሆኑን በደቡብ ኢጣልያ የምትገኘው የሲሲሊ ደሴት ዋና ከተማ ፓሌርሞ የሚገኘው ፀረ ማፍያ ምርመራ ቡድን መምሪያ አስታወቀ። የምርመራው ቡድን አክሎ እንዳመለከተው ግን፣ በተቀነባበረ እና በሕገ ወጥ መንገድ ሰዎችን የሚያዘዋውሩ ወንጀለኞች ለስደተኞቹ ሞት በዋነኝነት ተጠያቂዎች ናቸው። በዚህም የተነሳ የፓሌርሞ ፀረ ማፍያ ምርመራ ቡድን ስደተኞችን በሕገ ወጥ መንገድ ያዘዋውራል ብሎ በጠረጠረው አንድ ኢትዮጵያዊ ላይ በወቅቱ ምርመራ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ተኽለእዝጊ ገብረየሱስ

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ