1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያውያን ችግር በውጭ ሀገር

ሰኞ፣ መጋቢት 3 2004

ከሦስት መቶ የሚበልጡ ኢትዮጵያውያንና ደጋፊዎቻቸው ዛሬ በመዲናይቱ ኦስሎ አደባባይ ወጡ። ሰልፈኞቹ አደባባይ የወጡት በኖርዌይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ስደተኞች ማህበር የኖርዌይ መንግሥት በሀገሩ የሚገኙ ኢትዮጵውያን ተገን ጠያቂዎችን በቅርቡ በግዳጅ ወደ ትውልድ ሀገራቸው ለመመለስ የሚያስችለው አንድ ስምምነት ከሁለት ወራት በፊት

https://p.dw.com/p/14JVn
የኖርዌይ ጠቅላይ ሚንስትር የንስ ስቶልትንበርግምስል dapd

ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋ የተፈራረመበትን ተሳሳተ ያለውን ርምጃ ለመቃወም ባስተላለፈው ዓለም አቀፍ ጥሪ መሰረት ነው። ይኸው ከኦስሎ ማዕከላይ የባቡር ጣቢያ ተነስቶ በሀገሪቱ ፌዴራል ምክር ቤት አድርጎ ወደውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ያመራውን የተቃውሞ ሰልፍ ያዘጋጀውን የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ማህበር ምክትል ሊቀመንበር አቶ ፈቃዱ ብዙአየሁን ስልክ በመደወል በመጀመሪያ ስለሰልፉ ዓላማ እንዲያብራሩልን ጠይቄአቸው ነበር። አርያም ተክሌ

ይህ በዚህ እንዳለ፣ ባለፈው ሣምንት መጨረሻ በመዲናይቱ ቤይሩት የሊባኖሳዊ ጎልማሶች አንዲት ኢትዮጵያዊትን በሃገሯ ቆንስል መስሪያ ቤት ደጃፍ በኃይል ወደ መኪና ለማስገባት ጸጉሯ ይዘው መሬት ለመሬት ሲጎትቷት የሚያሳየው የሊባኖስ ቴሌቪዥን ያስተላለፈው አሳዛኝ ፊልም ኢትዮጵያውያንን አብዝቶ ያስቆጣ ሲሆን ድርጊቱን በጥብቅ አውግዘውታል። የሊባኖስ መንግስት የሰራተኛ ሚኒስትር ሳልም ጀርሳቲ መስሪያ ቤታቸው የስራና አሰሪ መስሪያ ቤቱንና ግፍ ፈጻሚውን ጎልማሳ ለጥያቄና ማስጠራታቸውንና በወንጀሉ ፈጻሚዎች ላይ ክስ እንደሚመሰረተም አስታውቀዋል፡፡ ጉዳዩን በቅርብ የተከታተለው ዘጋቢያችን ነቢዩ ሲራክ የተጎጅዋ ጤና በተረጋጋ ሁኔታ እንደሚገኝ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ነዋሪዎች በመጥቀስ አስታውቋል፡፡ ዘጋቢያችን የቆንስል መስሪያ ቤቱን ባለስልጣናትን ለማግኘት ያደረገው ተደጋጋሚ ሙከራ ባይሳካም በሊባኖስ ቤሩት የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ መስሪያ ቤት ሃላፊዎች፤ የሊባኖስ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናትና ነዋሪዎች ድጋፍ የሚሰጡትና ያንዳንድ ኢትዮጵያውያን አስተያየት በማካተት የሚከተለውን ዘገባ ልኮልናል፡፡

አርያም ተክሌ

ነቢዩ ሲራክ

ነጋሽ መሀመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ