1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ በኦስሎ፣ኖርዌይ

ሰኞ፣ መስከረም 29 2004

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ በዛሬው ዕለት በኖርዌይ መዲና ኦስሎ በሚካሄደው የኃይል አቅርቦት ተመልካች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አሁን እዚያው ይገኛሉ።

https://p.dw.com/p/RqB2
ምስል AP

የኖርዌይ መንግሥት እና ዓለም አቀፉ የኃይል አቅርቦት ጉዳይ ተመልካች ድርጅት በጋራ ያዘጋጁት ይኸው የሁለት ቀናት ጉባዔ የኃይል አቅርቦትን በተለይ በአዳጊዎቹ ሀገሮች ላሉት ለድሆች ማዳረስ የሚቻልበት ዘዴ እንዴት ሊሻሻል ይችላል ለሚለው ሀሳብ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየተወያየ ነው።የጉባዔው አዘጋጂዎች ብራዚል፡ ኢትዮጵያ፡ ሕንድ፡ ላይቤሪያ እና ደቡብ አፍሪቃ ይህንኑ ሀሳብ ተግባራዊ ለማድረግ በጀመሩት ጥረታቸው ላይ አብረው በአጋርነት እንዲሰሩም ጋብዘዋቸዋል። ጉባዔው በሚካሄድባት በኖርዌይ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን በኦስሎ ከተማ ጉባዔው በሚደረግበት አዳራሽ ደጃፍ በመሰብሰብ በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ አንጻር ተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል። የተቃውሞ ሰልፉን ያዘጋጀውን የኢትዮጵያውያኑን የግብረ ኃይል የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶክተር ሠይፉ ፀጋዬን አርያም ተክሌ በስልክ አነጋግራዋለች፤ በመጀመሪያም የተቃውሞ ሰልፉ ዓላማን እንዲያብራሩላት ጠይቃቸዋለች።

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ