1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ልዑካን የግብፅ ጉብኝት

ማክሰኞ፣ ኅዳር 11 2005

ከ30 በላይ የሚሆኑ እነዚህ አባላት ወደ ግብፅ የሚሄዱት በመገንባት ላይ ያለው የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ በግብፅ ላይ ምንም ጉዳት እንደማያደርስ ለማስረዳት ና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱንም ለማጠናከር መሆኑን የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል ።

https://p.dw.com/p/16mZp
ምስል DW/Azeb Tadesse Hahn

ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ኢዮጵያውያን ልዑካን በቅርቡ ወደ ግብፅ እንደሚሄዱ ተነገረ ። ከ30 በላይ የሚሆኑ እነዚህ ልዑካን ወደ ግብፅ የሚሄዱት በመገንባት ላይ ያለው የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ በግብፅ ላይ ምንም ጉዳት እንደማያደርስ ለማስረዳት ና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱንም ለማጠናከር መሆኑን መንግሥት አስታውቋል ። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚብሔር የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚብሔር

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ